ጠዳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ታሸገ

January 23, 2017

የልዑል አለሜ ዘገባ

በጎንደር ከተማ ጠዳ አካባቢ የሚገኘውን የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያንን ፅንፈኛው የትግራይ ነጻ አውጭ ቡድን ኮማንድ ፓስት ባዘዘው መሰረት ታሽጎአል ።

የሀይማኖት እባትችንና ምእመናንን ከሽብር ጋር በተይያዘ መልኩ በመክስስ በማንገላታት በማሳደድ በማሰቃየት እና በመግደል ያልታቀበው የትግራይ ነጻ እውጭው ቡድን በእስልምና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ እየፍጽመ በሚገኘው የግፍ መጠን በተዛማጁ የኦርቶዶክስ ቤተ እምነትን ለማፈረስ መጥረቢያውን ይዞ ከትነሳ ስነባብቷል።

የእምነት ተቋማትን እና አማኞችን በመናቅ ወደ ታላቅ ድፍረት የተሸጋገረው የህወሀት ጭንጋፍ ቡድን በዋልድባ እና ብዛት ባላቸው ቤተክርስቲያናት ላይ የፈፀመው የማን አለብኝነት ውንብድና እንዳለ ሆኖ ዛሬ ቤተ ክርስቲያንን ወደ ማሸግ ተሸጋግሮአል::

ይህን ተንትርሶ በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግቡብን በማለት ማስጥንቀቂያ የሰጡ ለነጻነት በመጋደል ላይ የሚገኙት ጀግኖቹ የጎንደር ትንታጎች በአንደነት ድምጻችውን ያስትጋቡ ሲሆን። በጠዳ ቅ/ግብርኤል ቤተ እምነት መታሸግ ምክንያት በጎንደር የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮችም ከክርስትና እምነት ትከታይ ውገኖቻቸው ባልተናነሰ ከፍተኛ ቁጭት እንደተሰማቸው እየገለጹ ይገኛሉ።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ 14/05/2009 በደቡብ ማርቆስ ስናን እንዲሁም አነብሴ አካባቢ ሲንቀሳቀስ የነበረ 218 የሚጠጋ ፀረ ሽብር እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ::

በአንድ ተውጣጭ ሀይል የተዋቀረውና በኮረኔል ቢሻው ጥላ የተመራው ፀረ ሽምቅ ቡድን በማርቆስ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሀይሎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም መወርወሩን በመርጅ የደረሱበት በስናን እና በአነብሴ አካባቢ የመሸጉ አርበኞች የትግራይ ነጻ አውጭው ቡድንን ድባቅ መተውታል::

Previous Story

Hiber Radio: በቋራ ለነጻነታቸው የሚታገሉትን ለማጥቃት የሔዱ የወያኔ ወታደሮች ያልጠበቁት ጉዳት ደረሰባቸው | በወሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በፌዴራል ፖሊሶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

Next Story

በወልቃይት ‹‹ዐማራ ነኝ››በማለታቸው ይቅርታ እንዲጠይቁ የተነገራቸው የሃይማኖት አባት ታሰሩ | በባሕር ዳር ለስብሰባ የተጠሩ ወጣቶች የብሔራዊ ውትድርና ግዳጅ እንዲሔዱ ተነገራቸው

Go toTop