Hiber Radio: ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ለአንባገነኑ ስርዓት ድጋፍ እየሰጠች መሆኗ እንዳስገረማቸው ገለጹ * በርሃብ ሳቢያ ከሰንኣ እስር ቤት ሊያመልጡ የሞከሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሞቱ የቆሰሉም አሉ * ሁለት ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው * የአውዳመት ገበያ ትንታኔ እና ሌሎችም….

April 13, 2015

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 4 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው አደረሳችሁ

< ...የመን ላለነው ኢትዮጵያውያን መፍትሄው በጋራ ሆኖ ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀልና የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ላይ ተጽዕኖ ማድረግ ነው… በሰንአ በእስር ላይ የሚገኙ ሰባት መቶ ኢትዮጵያውያን ያለ በቂ ምግብና ውሃ በከባድ ችግር ላይ ናቸው። ረሃቡን ለመሸሽ ከእስር ቤት ሊያመልጡ ብለው ሁለቱ በጥይት ተገድለዋል የቆሰሉትም የደረሱበት አልታወቀም...> ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሃይማኖት ከየመን ሰንኣ በዚያ ስላሉ ኢትዮጵያውያን ጠይቀን ከሰጠን ማብራሪያ

<… በአገር ቤት የበዓሉ ገበያ ከዓመት ዓመት እየጨመረ ነው … በዓል ለማክበር ተበድረህ ተጨንቀህ በዓል ባልመጣ ብለህ የምታከብር ከሆነ ምን በዓል ነው? ያብዛኛው ህዝብ ሕይወት ይሄ ነው ጥቂቶች ግን…> ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ ስለ አውዳመቱ ከአገር ቤት ጠይቀነው ከመለሰው (ሙሉውን ያዳምጡት)

<...የኦሮሞ ሕዝብ አንዱን ልጁን ከሌላው ስላበላለጠ ነው ሰይፈ ነበልባል ሬዲዮ ለኦሮሞ ሕዝብ እየሰራ በአቅም ማጣት የተዘጋው…>

ጋዜጠኛ እዮብ ባይሳ የሰይፈ ነበልባል ሬዲዮ አዘጋጅ የሬዲዮ ስርጭቱ መቋረጡን አስመልክቶ ጠይቀነው ከሰጠን ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡ)

የትንሳዔ በዓል አከባበር በቬጋስ (ቃለ መጠይቅ)

በፖሊስ ከጀርባው በተተኮሰበት ጥይት የተገደለው ጥቁር አሜሪካዊና የገዳዩን ድርጊት ያጋለጠው ቪዲዮ የቀሰቀሰው አዲስ ውይይት (ልዩ ጥንቅር)

ትንሳዔ( የባሻ ይገዙ -ልዩ ግጥም)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኢትዮጵያ እውነተኛ ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ ብቸኛው አማራጭ የሀይል እርምጃ ነው ሲሉ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሰሞኑን ለውጭ ሚዲያ ገለፁ

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላለው የግፍ አገዛዝ የምታደርገው ድጋፍ እንዳስገረማቸው ጠቁመዋል

በየመን በችግር ላይ ላሉ ኢትዮጵያውያን በውጭ የሚገኘው ወገን ህይወታቸውን ለመታደግ ለዓለም አቀፍ ቀይ መስቀልና ለዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ድምፃቸውን እንዲያሰሙ ተጠየቀ

በርሃብ ሳቢያ ከሰንኣ እስር ቤት ሊያመልጡ የሞከሩ ሁለት ኢትዮጵያውያን ሞቱ የቆሰሉም አሉ

የጣሊያን የባህር ጠባቂዎች 620 ኢትዮጵያውያንን ኤርትራዊያንን እና ሶማሊያውያን ስደተኞች የጫነች ጀልባን ከመስጠም አደጋ አተረፉ

ሁለት ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባቸው

የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ስደተኞች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በቸልታ አናልፍም ሲሉ አስጠንቅቀዋል

የአገር ቤት የበዓል ገበያ ዘንድሮም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሮ ዋለ

የኔቫዳ የሴኔት ኮሚቴ ሁበርን ወደ ስራ የሚመልሰውን የህግ ረቂቅ በሙሉ ድምጽ ለሴኔቱ አቀረቡ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Previous Story

የትንሣኤ ዋዜማ ቀጥታ መርሃግብር ከሚኒያፖሊስ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ (Live Stream)

Next Story

ኹራፋተ አምሳሉ ፡- መረጃና ማስረጃ አልባው እንቶፈንቶİ – ዲ/ን ዶክተር መሐሪ ወሰን /ከጅማ/

Go toTop