ዜና CMC ፍርድ ቤት ቢቢኤን የናንተው ድምፅ
– ኡዝታዝ አቡበከር አህመድ በችሎት ዳኞችን ሞገተ
– የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት በዛሬው እለትም ቀጥሎ የቀረውን የ28 ደቂቃውን የኦዲዬ – – ማስረጃ ጨምሮ 4 የሰነድ ማስረጃዎች ተደምጦዋል
– የህዝበ ሙስሊሙ አሚር ኡስታዝ አቡበከር አህመድ የተቃውሞ ንግግር አድርጎዋል
– የማረሚያ ቤቱ እንቢተኝነት የፍርድ ቤቱን ካንጋሮነት በግልፅ የሚያሳይ ነው ይሄ ደሞ በግልፁ የደህንነቶች እጅ እንዳለበት ያሳል ሲል አቤቱታውን አቅርቦዋል
ቢቢኤን ጥር 20/2007
በዛሬው እለት የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ዛሬ በዋለው ችሎ የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ከፌደራል ጉዳዬች ጋር ያደረጉትን ቀሪ የ28 ደቂቃውን ውይይት ጨምሮ 4 የሰነድ ማስረጃዎች ቀርበዋል::
የሰነድ ማስረጃዎች ከመቅረባቸው በፊት በህዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ተቃውሞ የቀረበ ሲሆን አምሳደሮቻችንን በመወከል የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢትዬጲያ ሙስሊሞች አሚር ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በነሱና በቤተሰቦቻቸው እየደረስ ያለውን ጫና አስመልክቶ ንግግር ያደረገ ሲሆን በአሁኑ ሳአት በማረሚያ ቤቱ እየደረሰብን ያለው ጫና ከኛም አልፎ በቤተሰቦቻችን ላይም ተጠናክሮ ቀጥሎዋል። ከዚህም በላይ በእምነታችን እየተሳለቁ ነው ባለቤቶቻችንና እህቶቻችን ሂጃባቸው እንዲተው እየተገደዱ ነው ለምን ብለን ስንጠይቅ ገና እናሰቃያችሃለን እያሉ የማአከላዊ ደህንነቶች መልክት እየላኩብነው ፍርድ ቤት መጥተን ተናግረን ስንሄድ ፍርድ ቤቱ ምን አቅም የለውም እያሉን ነው በርግጥም ለፍርድ ቤቱ አቤት ስንል ፍርድ ቤቱ ያንኑ ተጨባጭ ነው ያየንበት ቀድሞውኑ በግፍ ነው የታሰርነው በቃ ! አርፈን እንታሰርበት ስንተ ከኛ በላይ ወንጀል ሰርተዋል ተብለው የታሰሩ እጃቸው ላይ የጦር መሳሬያ የተገኘባቸው የትጥቅ ትግል ሲያደርግ የተያዙ እንኳን ይሄ እየደረሰባቸው አይደለም ስለዚ ይሄ ግፍና ጫና በአስቾኳይ ሊቆምልን ይገባል ብሎ የተናገረ ሲሆን ዳኛ ሊያስቆሙት ቢሞክሩም ልታስቆሙኝ አይገባም በማለት በማረሚያ ቤቱ እየተፈፅመባቸው ያለውን ጫናና በደል ለፍርድ ቤቱ በማስረዳት የፍርድ ቤቱን ካንጋሮነትም በሚገባ ሞግቶዋል::
በተጨማሪም አቃቢ ህግ መንግስት በኢቲቪ በኩል እያቀረበባቸው ያለውን የሀሰት ውንጀላ አስመልክቶ ለዛሬ ምላሽ እንዲሰጥ ተቀጥሮ የነበረ ሲሆን ቢሮዋችን ውስጥ መብራት ጠፍቶ ፕሪንት አላደረኩትም በማለት ይዞ እንዳልቀረበ ለፍርድ ቤቱ አስቂኝ ምላሹን ሰጥቶዋል::
ወኪሎቻችን ላቀረቡት የጭቆና አቤቱታ በመጨረሻ ብይን እንሰጣለን በማለት ዳኞቹ ትእዛዝ የሰጡ ሲሆን በሰጡት ትእዛዝ መሰረት በቅድሜያም በችሎቱ የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ከፌደራል ጉዳዬች ሲያደረጉት ከነበረው ወይይት ባለፈው ቀርቦ የቀረውን የ28 ደቂቃ ኦዲዬ ሲሆን በመቀጠልም የሰላም አንባሳደሮቹ የካቲት 26 ከመንግስት የተሰጣቸውን የመርህ ምላሽ ለህዝበ ሙስሊሙ ሪፓርት ያደረጉበትን ሂደት የሚያስረዳ የቪዲዬ ማስረጃ ቀርቦዋል።በስተመጨረሻም ሁለት ተከታታይ የቪዲዬ ማስረጃዎች የቀረቡ ሲሆን ሁለቱም በመዝገቡ 6ተኛ ተከሳሽ ለሆኑት ሸህ መከተ ሞሄ በማስረጃነት የቀረበ የካቲት 9 በመንግስት ያላቸውን ተስፋ ገልፀው የቀድሞውንእንዲሁም ስኔ 15 ደሞ የመጀሊስ አካላትን እኩይ ተግባራትንና የመንግስት ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነትን አስመልክተው ንንግር ያደረጉበትንና በዚሁ ንግግራቸው የመንግስትን ጣልቃ ገብነትን ለማረጋገጥ የመጀሊስ አካላት ለኮልፌ ቀራኔዬ ፓሊስ አባላት የ30 ሺ ብር ሽልማት ላደረገላቸው ድጋፍ እንደሰጠ ያጋለጡበትን የቪዲዬ ማስረጃ ለማየት ነው የተቻለው በዛሬው እለት ይቀርብ የነበረው ከፌደራል ጉዳዬች ጋር ወይይት ተደርጎበት የነበተው የክፍል 3 የኦዲዬ ማስረጃ ባለበት የድምፅ ጥራት ተስተካክሎ ለሌላ ጊዜ እንደሚቀርብ የተከሳሽ ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ በመግለፅ ዛሬ እንዲታለፍ በቃረቡት ጥያቄ መስረት ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ተደርጎዋል።
ችሎቱ በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን ጥርስ አልባው ካንጋሮ ፍርድ ቤት በቁርጠኝነት በስልጣን ደረጃ የበላዩ ለሆነው ማረሜያ ቤት ጠንከር ያለ ትእዛዝ ሰጥቶዋል።ማረሜያ ቤቱ መልስ ያልሰጠበትን በቂምክኒያት የማያቀርብ ከሆነ ከባድ የሆነ እርምጃ እኖስዳለን ሲሉ የማሀል ዳኛው የማይመስል ፋከራቸውን አሰምተዋል።
ችሎቱም በነገው እለት እንደሚቀጥልም ታወቆዋል::