ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
የህብር ሬዲዮ ጥር 10 ቀን 2007 ፕሮግራም
ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለጥምቀት በዓል አደረሳችሁ
<...ለሶስተኛ ጊዜ ጉባኤ አንጠራም ምርጫ ቦርድ ህገወጥ ተግባር እየፈፀመ ነው መኢአድ ላይ ምርጫው እንዳይሳተፍ የፖለቲካ ውሳኔ ተወስኗል እኛም የቀረን አንድ መንገድ ነው...እኛም የፖለቲካ ውሳኔ እንወስናለን....>
አቶ ማሙሸት አማረ የመኢአድ ሊቀመንበር የምርጫ ቦርድን ሕገ ወጥ አካሄድ በተመለከተ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
የጥምቀት በዓል በሎስ አንጀለስ ጃንሜዳ አከባበር (ልዩ ዘገባ)
የቀድሞ የመከላከያ ሰራዊትና የፖሊስ ሰራዊት አርበኞች ማህበር የቬጋስ ቻፕተርን በተመለከተ ቆይታ ከሻለቃ ማርቆስ መና ጋር (ሙሉውን ያዳምጡት)
ማርቲን ሉተር ጊንግ የነጻነቱ ታጋይ መታሰቢያ ልዩ ዝግጅት
አንድነት በሕገወጥ መንገድ ሊያፈርሱት የተነሱትን የህወሓት አገዛዝና ተላላኪውን የምርጫ ቦርድ በፍርድ ቤት የከሰሰው ፍርድ አገኛለሁ ብሎ ነው? ለምን በይፋ የፖለቲካ ውሳኔ በመወሰን ፓርቲው ለተለጣፊዎች ሳይሰጥ በፊት አልተንቀሳቀሰም? ለእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎቻችን የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ምላሽ ሰጥተዋል( ሙሉውን ቃለ መጠይቅ ያዳምጡ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የኤርትራና የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የአስመራና የአዲስ አበባ ገዥዎችን ለመጣል እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገለፁ
የአፋር ነፃ አውጭ ግንባር የኢትዮ ጅቡቲን የባቡር ሐዲድ አጠቃለሁ ሲል አስጠነቀቀ
በኢትዮጵያ የአፋሮችና የሱማሌ ተወላጆች የጎሳ ግጭት ዛሬም አላባራም ተባለ
እንግሊዝ መንግስት ለመናድ አሲረዋል በሚል በኢትዮጵያ ሶስት ዜጎቿ በእስራት መቀጣታቸውን ገለፀች
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ሁኔታን የሚቃኙ የእንግሊዝ የፓርላማ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ማሰባቸው ተነገረ
አቶ አንዳርጋቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር ከማይታወቀው እስር ቤት በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ
አንድነት በምርጫ ቦርድ ላይ በፍ/ቤት ክስ መሰረተ
መኢአድም ተመሳሳይ ክስ በቦርዱ ላይ ይመሰርታል
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አንድ የሱዳን ጄኔራል ኢትዮጵያን እንዲያጠፉ ሲያማክራቸው ሀሳቡን ተቃውመው እንደነበረ ለኢሳት ጋዜጠኞች ገለፁ
ኢትዮጵያና ኤርትራ በሰላም ለመኖር ወያኔ መወገድ አለበት ማለታቸውም ተገለፀ
የኔቫዳ ገቨርነር ብራያን ሳንዶቫል የ7.3 ቢሊዮን ዶላር ዕቅድ ለሁለት ዓመት ይዘው ቀረቡ
የ1.5 ቢሊዮን ዶላሩ ከታክስ ጭማሪ እንዲገኝ ህግ አውጭዎቹ እንዲያፀድቁላቸው ጠይቀዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉ