ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 135 ሰዎችን በሽብርተኝነት ክስ አሰረች

December 8, 2014

(ዘ-ሐበሻ) ሳዑዲ አረቢያ 135 ሰዎችን በሽብርተኝነት ጠርጥራ ማሰሯን አስታወቀች:: የሳዑዲ መንግስት እንዳስታወቀው በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ከታሰሩት 135 ሰዎች ውስጥ 109ኙ የራሷ ዜጎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 26 ሰዎች ከኢትዮጵያ; ከሶሪያ; ከየመን; ከግብጽ; ከሊባኖስ; ከአፍጋኒስታን; ከባህሬን እና ከኢራቅ ዜግነት ካላቸው መሆኑን ዘ-ሐበሻ ከሳዑዲ ሚዲያዎች ካገኘችው መረጃ መረዳት ተችሏል::

ከአክራሪዎች; ከአሸባሪ ቡድኖች; ከታገዱ የሽብር ኃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር, የነርሱን ዓላማ በማሰራጨት, ድብድብ በማንሳትና በሌሎችም ወንጀሎች የተከሰሱት ወገኖች ምን ዓይነት ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ሚድያዎቹ የገመቱት ነገር የለም::

በከተማ ውስጥ በሽብር ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት በፍጠር የተለያዩ የማቃጠል, የማፈንዳት, ሰዎችን በመግደል አንዳንድ ሽብር ወንጀሎች የተጠቀሰባቸው እነዚሁ ወገኖች ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እንደሚታይ ይጠበቃል::

የሳዑዲ ሚዲያዎች ከታሰሩት ውጥ ኢትዮጵያውያን ዜጎች እንዳሉበት ይግለጹ እንጂ ስለቁጥራቸው ብዛት ያሉት ነገር የለም::

Previous Story

Hiber Radio: የፈረንሳይ ባንክ የሕወሃትን አገዛዝ የ1 ቢሊዮን ዶላር የሶቨርኒ ቦንድን አላሻሽጥም አለ * ከ70 በላይ ኢትዮጵያውያን የተሳፈሩባት ጀልባ የመን ባህር ዳርቻ ሰጠመች

Next Story

ከብሔረሰብ በዓል ወደ ለታላቁ ሩጫ! – በእውቀቱ ስዩም

Go toTop