ለስድስት ጄነራል መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መሰጠቱ ተሰማ

October 14, 2014

ለስድስት ጄነራል መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መሰጠቱ ተሰማ:: መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች እንደዘገቡት ሶስት ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌተናንት ጀነራልነት ማዕረግ ሲሸጋገሩ ሶስት ብርጋዴር ጀነራሎች ደግሞ ወደ ሜጀር ጀነራልነት ተሸጋግረዋል፡፡

የጀነራል መኮንኖች ማዕረጉ የተሰጠው በወታደራዊ ግዳጅ አፈፃፀም፣ በስነ-ስርዓት አክባሪነ፣ በአሰራር ችሎታና ብቃት ብልጫ መሆኑን በሹመት ስነ ስርዓቱ ላይ መገለጹን የዘገቡት የመንግስት ሚድያዎች ከሙላቱ ተሾመ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መቀበላቸውን አትተዋል::

የሌተናንት ጀነራልነት ማዕረግ ያገኙት:-

1ኛ . ሜጄር ጀነራል አብርሃም ወልደ ማሪያም ገንዘቡ
2ኛ. ሜጀር ጀነራል አደም መሐመድ ሞሀመድ
3ኛ. ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ ናቸው::

የሜጀር ጄነራል ማዕረግ ያገኙት ደግሞ

1ኛ. ብርጋዴር ጄነራል ዘወዱ እሸቴ ወልዴ
2ኛ. ብርጋዴል ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ገብረስላሴ
3ኛ. ብርጋዴል ጄነራል ክንፈ ዳኘው ገብረስላሴ ናቸው::

Previous Story

ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም

Next Story

Health: የቁንጭና 101፡ ‹‹የቁንጅናሽ ግዙፍ ኃይል ያለው በውስጥሽ ነው›› – ‹‹The power be beautiful lies in you››

Go toTop