የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ የሰማያዊ ፓርቲን የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ደገፈ

May 14, 2013

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 29 2005 ዓም የአፍሪካ ህብረት የወርቅኢዮቤልዮ በአል በሚከበርበት ሰዓት ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ተከትሎ “የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ያለው የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ “ሰማያዊ ፓርቲ በመግለጫው የጠቀሳቸው አራት ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ መልስ እንዲያገኙ ከሚታገልላቸው ዋና ዋና የህዝብ ጥያቄዎች መካከል ውስጥ የሚገኙና ዘረኛው የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በዘረጋው የጭቆናና የግፍ መረብ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በግዴለሽነት በግልፅ በአደባባይ ከሚፈፅመው ስቃይ ፣ መከራና ፣ እንግልት ጥቂቶቹ በመሆናቸው ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሔራዊ ንቅናቄ ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረበው ወቅታዊና ተገቢ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪን ሙሉ ለሙሉ የተቀበለው መሆኑን በአፅንዎት ይገልፃል::” ሲል ባወጣው መግለጫ ላይ አስታወቀ።

ንቅናቄው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ህዝባዊ በመሆኑ ፤ በዚህ ዘረኛ የወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት ከልክ ያለፈ ጭቆና ፣ ረገጣና ፣ እንግልት ደርሶብኛል የምትሉ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ዜጎችና ፣ በምንወዳት ሃገራችን ለህዝብ የሚበጅ ቀና ለውጥን የምትመኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ፤ እንዲሁም ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ፣ የሃይማኖት ተቋማትና ፣ የሲቪክ ማህበራት ታላቅ ሃገራዊ ሃላፊነትና የህዝብ አደራ በጫንቃችሁ እንደተሸከማችሁ በመገንዘብ ፤ የሚጠበቅባችሁን ህዝባዊ ተልኮ መፈፀም ታሪካዊ ግዴታችሁ መሆኑን በመረዳት ፤ ከሰማያዊ ፓርቲ ህዝባዊ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ጎን እንድትቆሙ ሲል በጥብቅ እያሳሰበ ፤ ሃገራዊ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል:: የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ የሁሉም ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ጥሪ ነው!” ብሏል።

[gview file=”https://zehabesha.info/wp-content/uploads/2013/05/የሰማያዊ-ፓርቲ-ጥሪ-የሁሉም-ሃገር-ወዳድ-ኢትዮጵያዊ-ጥሪ-ነው.pdf”]

 

Previous Story

ሰውየው – ክፍል 1

Next Story

ዜና ዘ-ትግራይ (አብርሃ ደስታ ከመቀሌ)

Latest from Same Tags

የአብርሃ ደስታ የሰሞኑ ምርጥ ዘገባዎች

የህወሓት የኮብልስቶን ፖለቲካ (መቐለ) ======================== የመቐለ ወጣቶች (የዩኒቨርስቲ ምሩቃን) ተደራጅተው በኮብልስቶን ስራ ለመሳተፍ ቢወስኑም የህወሓት መንግስት ሊያስሰራቸው እንዳልቻለ ገለፁ። ወጣቶቹ በኮብልስቶን ስራ ተሰማርተው ስራ

ሁሉም ይናገር ሁሉም ይደመጥ!!

ከአንተነህ መርዕድ እምሩ በድሮ አጠራሩ ሻንቅላ በአሁኑ የጉሙዝ ብሄረሰብ የተማርሁት ትልቅ ነገር አለ። “በትልቆች ጉዳይ ምን ጥልቅ አደረገህ” እየተባልሁ በሚያሸማቅቅ ባህል አድጌ በጉሙዝ ህብረተሰብ
Go toTop

Don't Miss