የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ፣ በቅርቡ ኢትዮጵያን ከጎበኘው ከፍተኛ የውጭ ልዑካን ቡድን ጋር የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን
በተመለከተ በተደረገ ስብሰባ ላይ የተናገሩት፡፡ ግብፅ ሦስት ዓመት የደፈነውን የግድቡ ግንባታ እንዲቆም የምታደርገውን ውትወታ ትታ ወደ አቋረጠችው የውይይት መድረክ እንድትመለስ ያመላከቱት ሚኒስትር ዴኤታው የግድቡን ግንባታ ማቆም ጉዳይ መንግሥት ከማንም ጋር የሚደራደርበት አጀንዳ እንዳልሆነ አመልክተዋል፡፡
Source: ethiopianreporter.com