“ላገባ ነው” የተሰኘው የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ሜይ 28 በሚኒሶታ ይታያል

May 10, 2011

በወንዶች ጉዳይ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ፊልሞች ላይ የአተዋወን ብቃታቸውን ያሳዩት አክተሮች “ላገባ ነው” የተሰኘ የፍቅር ኮሜዲ ፊልም ሰርተዋል። በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ በሲኒማ ቤቶች እየታየ የሚገኘው ይኸው ላገባ ነው የተሰኘው የፍቅር ኮሜዲ ፊልም በሚኒሶታ ቅዳሜ ሜይ 28 ቀን 2011 በሴንትራል ሃይስኮል በ5፡30 ፒ.ኤም እንደሚታይ ታወቀ።
በቅርቡ ተሰርቶ ለዕይታ የበቃው ይኸው “ላገባ ነው” የተሰኘው የኮሜዲ ፊልም በሳቅ ባህር ውስጥ ጭልጥ አድርጎ የሚወስድ መሆኑን የሚመመሰክሩት ፊልሙን የተመለከቱ ሰዎች በአዲስ አበባ በርከት ያሉ የፊልም አፍቃሪያን ይህን አስቂኝ ፊልም ለማየት በየቀኑ እንደተሰለፉ ነው ብለዋል።
በሚኒሶታ ሜይ 28 “ላገባ ነው” ፊልም ሲታይ ከዚህ ቀደም በ”ቫኬሽን ፍሮም አሜሪካ” ፊልም የረኩት የስቴቷ የፊልም አፍቃሪያን በዚህም ፊልም እንደሚደሰቱ ይጠበቃል።µ

Previous Story

Adios! Oromay! Zenawi’s Ethiopia?

Next Story

ናቲ ኃይሌ ከዘ-ሐበሻ ጋር

Go toTop