
ብርቱካን ዛሬ በፖሊስ ተጠርታ ተጠይቃለች። በጥብቅ የደህንነትና የጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ወድቃለች። ማንም እንዳያገኛት ተደርጋለች። በፖሊስ ተጠርታ የተጠየቀችውን ጉዳይ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እየጠበቅን ነው። የሀዋሳና የአዲስ አበባ ከተሞች መታወቂያ ተዘጋጅቶላታል። አዲሱ ዲጂታል መታወቂያም ተሰርቶ ተሰጥቷታል። እየተዘጋጀ ላለው ዶክመንተሪ ፊልም ግብዓቶች መሆናቸው ነው።
አንዳንድ የኦሮሞ ሚዲያዎች ነገሩን አጡዘውታል። የብልጽግና ዲጂታል ሰራዊትም ጓዙን ጠቅልሎ እዚህ አጀንዳ ውስጥ ገብቷል። የልጂቱን ስም እያመነዠጉ መዋልና ማደር የሰሞኑ ተቀዳሚ ተግባራቸው አድርገውታል። በተለይ OMN የተሰኘው ሚዲያ ኩሽና ውስጥ ገብቶ ወሬ እየጠባበሰ ነው። የብርቱካንን ጉዳይ አንስቶ ‘የኦሮሞ ህዝብ ጥላቻ ተስፋፍቷል’ የሚል መርዛማ ፕሮፖጋንዳ እያሰራጨ ነው። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተበተነው የብልጽግና ሰራዊትም ፌክ ወረቀቶችን እየተቀባበለ የብርቱካንን በደልና ግፍ በማራከስ ላይ ተጠምዷል።
በእርግጥም የብልጽግናው መንደር ቅሌቱን ለመሸፈን እየተሯሯጠ ይገኛል። እንደጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ እየጮኸ ነው። በልጂቱ ግፍ ላይ ሌላ አሳፋሪ በደል እየጨመረ፥ የበለጠ ስነልቦናዊ ጉዳት እያደረሰባት ነው። እየተዘጋጀ ባለው ዶክመንተሪ ፊልም የውሸት ታሪክ እንድታጠና በማድረግ ልጂቱን ለማይጠገን የስነልቦና ስብራት እየዳረጋት ይገኛል። ጫንቃዬን ተገርፌ – ልብሴን ተገፍፌ። በበደል ላይ በደል። ምን ዓይነት እርግማን ነው?!
ይህ ጉዳይ የብልጽግናውን አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከጫንቃችን ላይ ለማራገፍ የሚያስችል የጋራ ቁጭት የሚፈጥር መሆን አለበት። በሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳ የሚሸፈን እውነት የለም። የአማራ ህዝብ ላነሳው የብረት ትግል ከዚህ በላይ ማስረጃ ሊቀርብ አይችልም። የብርቱካን ጉዳይ ከውቅያኖስ ላይ በጭልፋ እንደማንሳት ነው። ሚሊዮን በደሎች፥ አያሌ ግፎችና መከራዎችን የሚወክል እንጂ ብቸኛ ነጠላ ክስተት አይደለም። የፋኖን ትግል የምደግፈውም ለዚሁ ነው። የብልጽግናውን የግፍ ዘመን ለማሳጠር!
መሳይ መኮነን
“አንተ እራስህን ሲያምህ ከተሰማህ በሕይወት አለህ ማለት ነው..
ሌሎች ሲታመሙ አንተ ከተሰማህ ደግሞ በትክክል አንተ ሰው ነህ ማለት ነው”
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድህን
———————-