ነብይ ኢዩ ጩፋ ለቀረበበት ቅሬታ ምላሽ ሰጠ
“አንድ ነብይ በፓትሮል መታጀቡ አይግረማችሁ፣ መታጀብ ከፈለጋችሁ ስራ ስሩ”
ነብይ ኢዩ ጩፋ፤ ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ለተሰነዘረበት ቅሬታ በሰጠው ምላሽ፤ “አንድ ነብይ በፓትሮል መታጀቡ አይግረማችሁ፣ መታጀብ ከፈለጋችሁ ስራ ስሩ፣ የክርስቶስ አገልጋይ መጣ ሲባል ማርሽ ባንድ አይደለም ካላንደር ሁሉ ሊዘጋ ይችላል” ብሏል።
“ብታምኑም ባታምኑም በኢትዮጵያ ምድር በራሳቸው ጄት እየተንቀሳቀሱ የሚያገለግሉ አደገኛ ሰዎች ይነሳሉ” ያለው ነብይ ኢዩ፤ “ከዚህ በኋላ የሚኖሩ ፕሮግራሞች ከዚህ የበለጠ ይሆናሉ” ብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ካውንስል ባወጣው መግለጫ፤ ፖሊስ አገልጋዮችን ከማጀብ እንዲታቀብ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ አንድን አገልጋይ በጦር መሳሪያ ማጀብ እንደ ወንጌል አማኝ በፍፁም ተቀባይነት የሌለውና ከአስተምሮት ውጪ መሆኑን አስታውቋል፡፡