ቀደም ባለው ጊዜ በስራ ምክንያት ቡርጂ አካባቢ አንድ አመት ቆይቻለሁ። ጉጂዎችንንና ቦረናዎችን በቅርብ አውቄ ጓደኝነት መሰርቼ ኖሪያለሁ። እኔም እንደነሱ ወተት ወዳድ ነበርኩና ቅዳሜ ቅዳሜ ይዘዋት የሚመጧትን የቅል ወተት ለእኔ ለማቀበል አይኖቻቸው ሲንከራተቱ የማያቸው ጉጂዎችና ቦረናዎች ነገር ዘወትር ከህሊናዬ አይጠፋም። እኔ ኦሮምኛ አልችልም። እነሱ አማርኛ አይችሉም። ነገር ግን የሰው ልጅ ፍቅር ካለው የሚግባባበት ሌላ የሆነ ረቂቅ ነገር ያለው ፍጡር ነወ።
![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2023/02/331397943_1442832959818414_3141262873400492363_n-1-1-1.jpg)
![](http://amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2023/02/332459196_732870318391342_1532925833538991309_n-2-1-1.jpg)
በግለሰብና በቡድን መሞከሩ ውጤታማ አይሆንም። የሚሻለው ከዚህ በፊት በእርዳታ ስራ ልምድና ኔት ወርክ ያለውን ግሎባል አሊያንስን እንደግፍ። ዛሬ ይህንን ደብዳቤ ስጽፍ ወደ ግሎባል አሊያንስ መሪ ደውዬ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ እንደመከሩበትና ጎፈንድ ሊከፍቱ እንደ ሆነ ገልጸውልኛል። ሰለዚህ ሁላችንም በዚያ በኩል እናግዝ። ሌሎች አካባቢዎችም በተለይ ደብረ ብርሀን ከፍተኛ ተፈናቃይ አለና በዚያም በኩል ለወገን እንድረስ። እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ ይጠብቅ። አሜን።
ገለታው ዘለቀ