![](https://cdn.statically.io/img/amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/02/Meskerem-Abera.jpg?quality=100&f=auto)
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዛሬ ሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ/ም የደራሲና መምህርት መስከረም አበራን የዋስትና መብት ተጠብቆ ከእስር እንድትፈታ መወሰኑን ጠበቃዋ ሄኖክ አክሊሉ ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ።
ዛሬ የዋለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በፖሊስ የቀረበውን የመስከረም አበራ የዋስትና ውሳኔ ይሻርልኝ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ከትናንት በስትያ ሰኞ ሰኔ 6 ቀን 2014 ዓ/ም መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንድትፈታ የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶታል። ባለፈው ሰኞ ሰኔ 6ቀን 2014 ዓ/ም መስከረም አበራ፤ በ30 ሺህብር ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የስር ፍርድ ቤት የወሰነ ቢሆንም ፖሊስ ውሳኔው ይቀልበስልኝ ሲል ይግባኝ ጠይቆበት ነበር። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 7 2014 ዓ/ም ፖሊስ ያቀረበውን የይግባኝ አቤቱታ የተመለከተው ፍርድ ቤት ይግባኙን ውድቅ በማድረግ የዋስትና ውሳኔውን አፀንቶት ነበር። ነገር ግን ፖሊስ እንደገና ሰበር ሰሚ ፍርድቤትን ይግባኝ በመጠየቁ የፍርድ ቤቱ በውሳኔ ተግባራዊ ሳይሆን መቅረቱን የአዲስ አበባዋ ወኪላችን ሃና ደምሴ ዘግባለች።
በደራሲና መምህር መስከረም አበራ የዋስትና ውሳኔ ላይ ፖሊስ ያቀረበው አቤቱታ ውድቅ ሲሆን የዛሬው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ለሁለተኛ ግዜ ነው ።
የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ” ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ” ወንጀል ተጠርጥራ ግንቦት 11 2014 ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዛ ከአንድ ወር በላይ በእስር ላይ ቆይታለች።
DW ፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ/