በምዕራብ ሸዋ ዞን የዳኖ ወረዳ ነዋሪዎች የአሸባሪው ሸኔን የጥፋት ድርጊት ተቃወሙ

April 27, 2022
በምዕራብ ሸዋ ዞን የዳኖ ወረዳ ነዋሪዎች የአሸባሪው ሸኔን የጥፋት ድርጊት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል።
የሸኔ ቡድን በወረዳው የሕዝቡን ንብረት በመዝረፍ እና የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት በከንቱ በመቅጠፍ ኅብረተሰቡን አደጋ ላይ መጣል ከጀመረ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል።
ይህ ድርጊት ያማረራቸው የዳኖ ወረዳ ነዋሪዎች በአንድነት በመውጣት ሸኔን የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ መንግሥት በሽብር ቡድኑ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚደግፉ እና ኅብረተሰቡን መሸሸጊያ ያደረጉ አባላቱን ለማጋለጥ ዝግጁ መሆናቸውን አሳይተዋል።
(ኢ.ፕ.ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ኋላ-ቀር አስተሳሰብ ባላቸውና በአረመኔዎች የሚመራ ምስኪን ህዝብና አገር! – ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)

Next Story

በጎንደሩ ግጭት የበርካታ ሰው ህይወት ጠፋ

Go toTop