![](https://cdn.statically.io/img/amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/04/277748030_5230720110283453_128322484686513920_n.jpg?quality=100&f=auto)
ዜና ቲዩብ አንድ መምህርን ጠቅሶ እንደዘገበው በአንድ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራንና አመራሮች ጋር በተደረገ ስብሰባ ላይ የት/ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተገኝተዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ሚ/ሩን ወደ መድረክ ሲጋብዟቸው “የተከበሩ…” ይሏቸዋል። ፕ/ሩም ንግግራቸውን ሲጀምሩ “ማንም የተከበረ የለም። ትውልድና ሃገር እየገደሉ የተከበሩ መባል የለም። ምናል መስዋዕትነት ከፍለን መጪውን ትውልድ ከሞት የታደግን ከሆነ እነሱ የተከበሩ ሊሉን ይችላሉ” ይላሉ። ቀጥለውም የትምህርት ስርዓቱን መበስበስ ምክንያቶች በዝርዝር ከተናገሩ በኋላ የዩኒቨርሲቲው መምህራን የመፍትሄ ሃሳብ እንዲያቀርቡ ጠየቁ።
ከቀረቡት ሃሳቦች ውስጥ 99% የቤት መስሪያ ቦታ እና የመኪና መግዣ ብድር ጥያቄ ነበር። ሚኒስትሩም ይህን ሲሰሙ በብስጭት ዩኒቨርሲቲውን ጥለው ሄዱ። ይላል ደረጀ ሃ/ወልድ በዘገባው።