Live

የትግራይ ክልል ተፈናቃዮች በቆቦ

March 19, 2022

ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው በሰሜን ወሎዋ ቆቦ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የተጠለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች በምግብና በመሰረታዊ ድጋፍ አቅርቦት መቸገራቸውን ገለጹ።

በመቶዎች የሚቆጠሩት ተፈናቃዮች በትግራይ ክልል ባለው የምግብና የፀጥታ ችግር ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተፈናቅለው ወደ ቆቦ መግባት ከጀመሩ ሁለት ሳምንት እንደሆናቸው ተነግሯል።

የራያ ቆቦ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ከትግራይ ክልል ተፈናቅለው የመጡት ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ መደበኛ የወንጀል መከላከልና ጸጥታ የማስከብር ሥራው ላይ ተፅዕኖ እንዳሳረፈበት ገልጿል። ጽ/ቤቱ የክልሉና የፌዴራል መንግሥቱ ተፈናቃዮቹን ወደ ሌላ ቦታ እንዲያንቀሳቅስ ጠይቋል።

የትግራይ ክልል የውጭ ግንኙነት አስተባባሪ መሆናቸውን የሚናገሩት ካናዳ የሚገኙት አቶ ዮሃንስ አብርሃም ነዋሪዎች ከቀናት በፊት ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት የስልክ ምለሽ ከቤተሰብ ጋር ለመገናኘት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጭ ምግብ ፍለጋ እንደስደተኝነት ሊመደብ የሚችል የሚታወቅ እንቅስቃሴ እንደሌለ ገልፀው ነበር።

VOA

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ለትልቁ ሰው፤ መድኃኔዓለም አቤት ብያለሁና፣ መልሴን እጠብቃለሁ!! – በዲ/ን ተረፈ ወርቁ

Next Story

ብሔራዊ ምክክር፣ ምንነት፣ ዓላማው፣ ይዘቱና አፈጻጸሙ – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Go toTop