የትምህርት ሚኒስቴር ከ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል

March 18, 2022

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ፒ ኤች ዲ) ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል ፈተና በሁለት ዙር እንዲሰጥ መደረጉንና በመጀመሪያው ዙር የስነ-ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ከፈተናው ቀን ቀድሞ በመውጣቱና የውጤት ግሽበት በመምጣቱ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከወሠዱት 544ሺ 682 ተማሪዎች ውስጥ 44 ከመቶዎቹ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በሁለተኛው ዙር ከተፈተኑት 53ሺ 997 ተማሪዎች ውስጥ 28 ከመቶዎቹ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር 554 ሺ 682 ተፈታኞች ውስጥ ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ይመደባሉ ብለዋል።

የ 10ኛ ክፍል የማትሪክ ፈተና በመቅረቱ ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አራት ዩኒቨርሲቲዎቻችን መቀበል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምናው የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን አብራርተዋል።

በትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውና ዘንድሮም ይመደቡ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ 48ሺ ተማሪ የቅበላ አቅም አጥተናል ብለዋል።

ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በ43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 152 ሺ 14 ተማሪዎች እንዲመደቡ መደረጉና ይህም ከአምናው የቅበላ አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

ፀጥታ ችግር ያጋጠማቸው አከባቢዎች በተመለከተ የተለየ መቁረጫ ነጥብ ለመወሰን የሚያስገድድ የውጤት ትንተና ስላልተገኘ በበመደበኛው የመቁረጫ ነጥብ ተስተናግደዋል ብለዋል።

ባለፈው አመት በ47 ዩኒቨርሲቲዎች 147 ሺ ተማሪዎች ምደባ የተደረገ ሲሆን ዘንድሮ በ43 ዩኒቨርሲቲዎች 152ሺ 014 ተማሪዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

በኢትዮጵያ…ከ3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 65 በመቶው ማንበብ አይችሉም፤

Next Story

በመተሐራ ከተማ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ

Go toTop