![](https://cdn.statically.io/img/amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2022/03/275846325_2790061484634435_4749141181291664791_n.jpg?quality=100&f=auto)
–
በዚሁ ምክንያት ከባህር ዳር ጎንደር ዛሬ ከጧት ጀምሮ ትራንስፖርት ተቋርጦ ውሏል::
–
የአማራ ልዩ ሀይል ከተለያዩ ግንባሮች በክልሉ መንግስት በቂ ድጋፎች እየተደረገላቸው ባለመሆኑ ሰላም የማስከበር ስራ አንሰራም በማለት ለክልሉ መንግስት ቅሬታ ለማቅረብ ወደ ባህር ዳር እየተጓዙ ባለበት ወቅት አዲስ ዘመን አካባቢ ከመንግስት አካላት በቀረበላቸው ጉዳዩን በውይይት እንፍታው የሚል ጥያቄ መሰረት ውይይት እያካሄዱ በመሆኑ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ የአዲስ ዘመን ከተማ ብልጽግና ሀላፊ አቶ ምስጋናው ማስረሻ ለአሻራ ሚዲያገልጸዋል::
–
ሀላፊው ለትራንስፖርት መቋረጡ በምክንያትነት ያነሱት ለቅሬታ ከመጡ የልዩ ሃይል አባላት ጋር የሚደረገው ውይይት አስፓልት ላይ በመሆኑ ነው የሚል ምላሽ ሰጠዋል::
–
ውይይቱ ለሁለት ቀን ያክል አስፓልት ላይ እየተካሄድ መሆኑን በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ተኩስ ተከፈተ የሚባለው ወሬ ውሸት ነው ሲሉም ተናግረዋል ::
አሻራ ሚዲያ