አሸባሪው ሕወሓት የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አማራ ክልል ገብተዋል

March 15, 2022

 

 

አሸባሪው ሕወሓት የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በአጎራባች የአማራ ክልል ከተሞች መጠለላቸው ተገለጸ።

የኢፕድ ዘጋቢዎች በቦታው በመገኘት እንዳረጋገጡት የአሸባሪውን ቡድን ግፍና ጭቆና በመሸሽ በቆቦ ከተማና አካባቢው ብቻ በ 3 መጠለያ ጣቢያዎች በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች በመንግስት የዕለት ደራሽ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው።
በሰቆጣም በተመሳሳይ በርካታ የክልሉ ተፈናቀዮች ከመንግስትና ከህዝብ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን፤ በየቀኑ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ የትግራይ ክልል ስደተኞች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ አጎራባች የአማራ ክልል አካባቢዎች እየተሰደዱ መሆኑን ዘጋቢዎቻችን አረጋግጠዋል።
ተፈናቀዮቹ የሕወሓት አመራሮችና ታጣቂዎች በሕዝቡ ላይ ዘግናኝ ግፍና በደል እየፈፀሙ መሆናቸውንም አጋልጠዋል።
ዘጋቢዎቻችንን ተፈናቃዮችን ጠቅሰዉ እንደዘገቡት፤ የክልሉ ህዝብ በረሃብ እንድይጎዳ ከኢትዮጵያ መንግስት የሚላከውን እርዳታ የሽብር ቡድኑ በመከልከልና ረሃቡን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለዳግም ጦርነት አስገድዶ እየመለመሉበት መሆኑን አረጋግጠዋል።
የቆቦ ከተማ ሰላምና ደኅንነት ጽሕፈት ኃላፊ ሀምሳ አለቃ አበበ ደርሶ ጉዳዩን አስመልክቶ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ እስካሁን በቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች አሉ።
አሁንም ወደ ከተማው እየመጡ ያሉ ዜጎች ከከተማው አቅም በላይ ስለሆነና እውነተኛ ተፈናቃዮችን መርዳት እንዲቻል ተፈናቃዮቹ በሀብሩ ወረዳ ወደሚገኘው ጃራ አካባቢ ለመውሰድ ሁኔታዎች እየተመቻቹ ነው፤ ለተፈናቃዮች መጠለያ የሚሆኑ ድንኳኖች፣ የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች፣ ምግብ፣ አልባሳትና ሌሎችም መገልገያ ቁሳቁሶችም ተዘጋጅተዋል ብለዋል።

በአብዱረዛቅ መሀመድ (ራያ ቆቦ)

(ኢ ፕ ድ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከልክሏል! # አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያለው ልብስም ተከልክሏል!

Next Story

ጦርነቱ የአሜሪካንና የአውሮፓውያን ነው ! ጦርነቱ ራሺያን ለማውደም የታለመና ይህንን ዕቅድ ለማክሸፍ የሚካሄድ ጦርነት ነው!

Go toTop