ኃያላን ሆይ የእግዘብሔርን አይን እንዳትወጉ ተጠንቀቁ ! – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

January 31, 2022

ዛሬና አሁን ፤ ከመቅፅፈት   ” የሦሥተኛው የአለም ጦርነት ይጀመራል ። ” እያልን እየሰጋን ነው ። ” ሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ ፣ አራተኛ ብሎ ነገር የለም ። ” ከተባለ ቆየ ። ይኽ  የተባለው አቶሚክ ቦንብ ፣ ከተፈለሰፈበት ጊዜ ጀምሮ ነው ። ከዛ በኋላ ደሞ  የኒኩለር መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል ተብሎ በመፈራቱ ነው ። ሥለሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ካወራን አራተኛ ብሎ ነገር እንደሌለ እንረዳ ። የተባለው ። እናም ሦሥተኛው የዓለም ጦርነት ሁለተኛ ዕድል ለሰው ልጆች እንደማይሰጥ ተገንዘብ ።ሦሥተኘው የዓለም ጦርነት ከተጀመረ  ደግሞ  ሰው በራሱ ጥበብ ፣ በጅልነቱ ግዝፈት መጥፋቱ ሳይታለም የተፈታ ሃቅ ይሆናል ።

ከዚህ  እውነት አንፃር ፣  በቀድሞዋ የሶቬት ህብረት አካል ፣ በዩክሬን ሰበብ የሚጀመር ጦርነት ካለ ፣ ፍፃሜው ፣ የዋሽንግተንም ፣ የክራሚልን ና የምዕራብያኑን ጥፋት ማሥከተሉ የተረጋገጠ ነው ።

እናም ኃያላኑ ከእብሪት ሃሳባቸው ለሠከንድ ቆም ብለው እንዲያስቡ እንመክራለን ።እባካችሁ ፣ ለመዋጋት ያሰባችሁት የኒኩለር ጦር መሣሪያ ከታጠቀ ኃይል ጋራ ነው ። ኔቶ ቢሰባሰብ ፣ አሜሪካ ኒቶን ብትደግፍ ፣ ነገሩ “ ተልባ ቢጫጫ ፣ በአንድ ሙቀጫ ነው ። “    ይኽንን መገንዘብ  ከልተገባ አካሄድ መራቅ ራሥን ማቀብ ያሥችላል  ።

ኒቶም ሆነች አሜሪካ ለዩክሬን ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ፣ ለራሳቸው ጥቅም ብለው ነው  ፤ “ ያዙኝ ።  ልቀቁኝ !  በማለት ለገላጋይ የሚያሥቸግሩት  ። ራሻ ግን የደህንነት ሥጋት ሥላለባትና በአሜሪካኖች የተነሳ ያቃጠላትን እና ግዛቶን ወደ 15 ትንንሽ ግዛት ትልቅየዳረገውን ትልቅ  ጠባሳ በማየት ሁሌም መቆጨቶ ተገቢ ነው  ። …

በሲአይ ኤ ተንኮል የቀድሞዋ ሶቬት ህብረትከ 1988 እኤአ ለሦሥት ተከታታይ ዓመታት  ሥትገዘገዝ ሠንብታ ፣   ከ ዴሰምበር 31/ 1991  ጀምሮ 15 ቦታ መሸንሸኖንም ሞስኮ አትዘነጋም   ።  የእኛም የሶሻሊዝም ሥርዓት ከሶቬት ህብረት መፍረስ ጋር በ1983 እንዳልነበረ መሆኑን አሥታውስ ። ደጋፊና ተከላካዩ የነበረችው አገር በመፈራረሶ ደርግና የሶሻሊዝም ሥርዓቱ እንደ ኩይሳ በቀላሉ   መፈረካከሱንም ተረዳ ።

ታላቋ ሩሲያንም ሆነ ፣ አገራችንን በምሥጢራዊ ሤራ ያፈራረሰው ሲአይ ኤ ከኬጂቪ በቴክኖሎጂ ና በዘዴ በልጦ ነው ። እርግጥ የነ ጎርባቾቭና የነየልሲን የዋህነትም ሲአይኤን አግዞታል ። በዛ ላይ በመንግሥት ውሥጥ የነበረው ሙሥና ህዝቡን ከኢኮኖሚ አንፃር ጎድቶት ነበር ።

ዛሬ ግን ይኼ ሤራ በራሻ ላይ ሊተገበር አይችልም ። ራሻ በህዝብ እጅግ በጣም ቅቡልነት ያለው መንግሥት ነው ፤  ዛሬ ያላት ። እናም ሲአይኤ በህዝብ ብሶት ሊጠቀም አይችልም ። ደሞም ኬጂቢ ና ሲአይ ኤ በአቻ ቴክኖሎጂ ሥለሚጠቀሙ የሲአይኤን የሴራ መንገድ ኬጂቪ ደቂቃ ሳይሞላ ሥለሚያውቀው እንደ ቀድሞ መበለጥ አይኖርምና በዩክሬን የኔቶም ሆነ የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ዋጋ ስለሚያሥከፍል ፣ ኔቶም ሆነ አሜሪካኖች ለአለም ሰላም ሲሉ ከዩክሬን ቢወጡ መልካም ነው ።  አሜሪካኖች ከሩሲያኖች የበለጠ ለዩክሬኖች ዘመድ አይደሉም ና ይህ የእልህ መንገድ ለአሜሪካ ና ለአውሮፓ ህዝብ እንደማይጠቅም አውቀው ከዩክሬን ቢወጡ ይመረጣል ። ሩሲያም ሆነች ዩክሬን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው ። የሁለቱም ቋንቋ ሩሲያውኛ ነው ። ባህላቸውም ተመሳሳይ ነው ።

ለአንተ ለወገኔ ለአገሬ ልጅ ደሞ የምልህ አለኝ ።ወዳጄ ሆይ ! ሲአይኤም ሆነ ኬጂቢ ዛሬ የሚጠቀሙት ዘመናዊውን ቴክኖሎጂ በመሆኑ ሤራቸውን እንዲህ በቀላሉ አትደርስበትም  ።  ኬጂቢ የሲአይኤን ሴራ እግር በእግር ተከታትሎ የሚደርስበት በቴክኖሎጂው ረቂቅነት ነው ። አቻ ቴክኖሎጂ አለዋ ። አውሮፓም ሆነ አሜሪካ ፣ ዩክሬን በከርሰ ምድሮ ባላት ሀብት ጎምጅተው ነው ይኽንን የ43 ሚሊዮን ህዝብ አገር አለንልህ የሚሉት ።

ዩክሬን በመአድን የበለፀገች አገር ናት ። የዲንጋይ ከሰል ክምችቶ እጅግ ግዙፍ ነው ። የብረት ክምችቶሞ የዛን ያህል ኘው ። በነዳጅ ሀብቷም ትታወቃለች ። የሚነራል ሀብትም አላት ። ሰልፈር በብዛት የሚመረተው ከዩክሬን ነው ። የቀረውን ዊኪፒዲያን ጠይቀህ ተረዳ ።

የእኛ አገርንም ብጥብጥ ና የነሱን ጣልቃ ገብነት ከዚህ አንፃር ተረዳው ።እኛ ገና አዳጊ አገር በመሆናችንም የነሱን ድጋፍ እንደምንሻ ተገንዘብ ።  ። ደሞም ሩሲያም ሆነች አሜሪካ ፤ ሁለቱም ከዓለም የደበቁት የረቀቀ የመረጃ መሰብሰቢያ የቴክኖሎጂ መሣሪያ ሊኖራቸው እንደሚችል ተረዳ ። “እባብ  ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ  ” ነው ። ነገሩ ። በዓለም  ምን እየተከናወነ እንዳለ  ፣ ሲአይኤም ፣ ኬጂቢም ፣ ሞሳድም በሰከንድ ውሥጥ ያውቃሉ ።

ወደ  ሰማይ ቀና ብለህ ተመልከት ። ምንም አይታይኽም ?  አዎ አይታይኽም ። እኔም የሚታየኝ ነገር የለም ። ሣተላይቶቹ እኮ  በጨረቃ ሙሁዋር ውሥጥ ነው የሚሽከረከሩት  ። እንዴት ልታያቸው ትችላለህ ። ነገሩ ያለው በምድር መቀበያ መሣሪያው ውሥጥ ነው ። እሱን ደሞ ለአንተ አይሰጡኽም ። የፔንታጎን ፣ የክሪሚሊን ፣ የቴልአቪቭ ጉዳይ ነው ። እናም የዙሆኖቹ መጣላት አንተን ሣሩን እንደሚጎዳህ ፣ በመገንዘብ ይኽንን የጥጋበኞች ጦርነት አውግዝ ። እውቀቱ ፣ ቴክኖሎጂው ና ብልሃቱ አለን ፤ በማለት እጅግ ወደ ሰማይ ሥትንጠራሩ የእግዘብሔርን አይን እንዳትወጉ ተጠንቀቁ  ግን በላቸው ።

 

……

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

Part 20 -ሁለት መቶ ሺ!፣ የመጨረሻው መጀመሪያ? እና የክትባት ግዴታ – ፀጋዬ ደግነህ (ዶ/ር)

Next Story

መንግስት ከህወሀት ጋር ድርድር እያደረገ እንደሆነ እየሰማን ነው – መሳይ መኮነን

Go toTop