በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው 62 ግለሰቦች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል

January 7, 2022
የፍትህ ሚኒስቴር ዛሬ አርብ ታህሳስ 29 ምሽት ባወጣው መግለጫ፤ በእነ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ስር ያሉ 20 ተከሳሾች እና በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ስር ያሉ አራት ተከሳሾች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አስታውቋል። የተከሳሾቹ ክስ እንዲነሳ የተደረገው “ሃገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ በማሰብ” መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በተመሳሳይ ሁኔታ በእነ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው 62 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ውስጥ የስድስት ግለሰቦች ክስ እንዲነሳ መደረጉን ሚኒስቴሩ በዛሬ ምሽት መግለጫው ጠቅሷል። “የጤና እና የዕድሜ ሁኔታቸውን ከግምት በማስገባት” ክሳቸው እንዲነሳላቸው የተደረጉት አቶ ስብሐት ነጋ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አቶ አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር እና ወ/ሮ ኪሮስ ሐጎስ ናቸው።
በእነ ጃዋር መሐመድ እና ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ የተካተቱ ተከሳሾችን ማንነት ለመመልከት ከታች የተያያዙትን ምስላዊ መረጃዎች ይመልከቱ።
(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

እስክንድር፣ ጃዋር፣ በቀለ ገርባና ስብሃት ነጋን ጨምሮ በእስር ላይ የነበሩ የፖለቲካ መሪዎች በምህረት ተፈቱ

Next Story

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የኖቤል የሰላም ሽልማትን ያጽድቁ ወይም ይሻሩ

Go toTop