ለምን ….ለምን…..“በቃ” ? – ማላጂ

December 29, 2021

በቃ የሚለዉ ቃል እንደ እኛ አገር ኢትዮጵያ  የተሰኘች የዕኛዉ የሀበሻ ምድር በስነ ፍጥረት ታሪክ ጋር የተፈጠረ ጠቅላይ ቃል ሆኖ  “ዕምቢ” ማለት ነዉ ፡፡

ስለ በቃ በግሪክ ቋንቋ የተፃፈ …..የሚል ካለ እርሱ ከዉስጥ ይልቅ በዉጭ ጥገኝነት አባዜ ሩቅ ናፋቂዎች የሚሉት ካለ ……..እገሌ እናዳለዉ  ማለት ይቻላል፡፡

በቅርቡም ከአንድ ዓመት አስቀድሞ በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ  በጊዜዉ አጠራር የዓማራ ክልል ህዝብ እና ወጣት ለአለፉት የስቃይ እና አሳር ዘመናት ፳፯ ዓመት የነበረዉ የአገር ዉስጥ መፈናቀል፣ የአስተዳደር በደል እና ማግለል ፣ ጂምላ ፍጂት ፣ ስደት ፣ ዉርደት ፣አድርባይነት እና አድሎዋዊነት……“በቃ ” ማለቱን መርሳት ዘበት ነዉ ፡፡

ለዚህም ለዓማራ ወጣት እና ህዝብ ጆሮ ሰጥቶ ተገቢዉን ትኩረት እና ምልሰት አለመስጠት እና ከዚያ በተቃራኒዉ በመንግስት የተሰጠዉ ምላሽ ምን እንደነበር የትናንት ትዉስታ ነዉ ፡፡

የዓማራ ህዝብ እና የመላዉ ኢትዮጵያ ልጆች  እየሞቱ መኖር ሳይዉል ሳያድር አገር ሞት የሚያስከትል ስለመሆኑ ከዘመናት መከራ የተማረዉ ህዝብ በተለይም የዓማራ ወጣት  የህልዉና ስጋት  ከቁጥጥር ዉጭ ከመሆኑ እና ከባሰ ብሄራዊ ቀዉስ ለመዳን ሰሚ ያለዉ ይስማ ብሏል፡፡

ራስን ፣ ህዝብን እና አገርን ከጥፋት ፤ህዝብን ከሞት ለመታደግ እንደራጂ ፣ እንተባበር ፣ እንታጠቅ ፤በህብረት እና በአንድነት ዘብ ዕንቁም …… ሞት በቃ  ያለዉ  ለ፴ ዓመታት የነበረዉን በራስ አገር ምድር በአድሎ እና መድሎ  ህዝብን በራሱ አገር እና ምድር ባይተዋር የሚያደርግ፣ ጅምላ ፍጂት ፣  ስደት እና ድህነት በመላ ኢትዮጵያ “ በቃ” ነበር ያለዉ ፡፡

ዛሬ“ በቃ” (Enough is enough  )ስንል ለባለቤቱ ዕዉቅና ሰጥተን  ለዉጭ እና ለዉስጥ የሞት እና ባርነት ነጋዴዎች ብቻ ሳይሆን ለአለፉት የመከራ ዘመን ህዝብን እና አገርን በባርነት እና በግዞት ይዘዉ ህዝብ ሲያሰቃዩ ፣ ሲያደሀዩ ፣ ሲያገሉ ፣ሲገድሉ እና ሲያስገድሉ…..የነበሩት ዛሬ የህዝቡን  በቃ  ጥያቄ   ያልተፈለገ ይዘት እና ዓይነት እንዲኖረዉ እያደረጉ ነዉ ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና ኢትዮጵያ  በቃ ያሉት እና የሚሉት በዉስጥ እና በዉጭ የነበረዉን እና ያለዉን  ሁሉን አቀፍ መድሎ እና አድሎ የዉስጥ  አስተዳደር መርህ ከስሩ በመንቀል ድህነት፣ ሞት ፣ ስደት ፣ዕንግልት፣ ባርነት( ባይተዋርነት)፣ መፈናቀል….ነበር ነዉ ፡፡

ለሁላችን አገር እና ምድር ዘላቂ  ዕድገት እና የህልዉና አስተማማኝነት ለዕዉነት እና ለብሄራዊ ማንነት ዕዉቅና መስጠት ያስፈልጋል፡፡

በቃ ሲባል  አፍስሶ ከመልቀም የህልም ሩጫ ከማድረግ በላይ ተፈጥሯዊ ፣ሰባዊ እና ብሄራዊ መብቶች  እና ትሩፋቶች ያለምንም ገደብ እና ቅድመ ሁኔታ ሊከበር፣ ሊተገበር እና ሊኖር ይገባል፡፡

በቃ የምንለዉ የዉጭ ጠላቃ ገብ የዉስጥ ጠላቶችን ሞግዚት ብቻ ከሆነ እንደ በበቀን ጮኾ ታጥቦ ጭቃ ከመሆን ያለፈ  ግንጥል ጌጥ  ከተደጋጋሚ ስህተት የማያመልጥ ከንቱ ጩኸት ይሆናል  ፡፡

ማላጂ

“አንድነት ኃይል ነዉ ”

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ከለንደን እስከ እትዮጵያ የተዘረጋው የወንጀለኞች ቡድን /ስኳድ/ ዕቅድና የማስፈራራት ዘመቻ

Next Story

በአሁኑ ሁኔታ የአማራንና የአፋርን ነዋሪ ደህንነት መከላከል የሚቻለው በዋናነት በትግራይ ውስጥ የመከላከያ ዞን ሲኖር ነው

Go toTop