አሸባሪው የሕወሓት ወራሪ ቡድን የአለዋ ድልድይን ጨምሮ በርካታ መሰረተ ልማቶችን እያወደመ ሄዷል፡፡
ወራሪው ኃይል በአለዋ ድልድይ ላይ ያደረሰውን ጉዳት በዘላቂነት ለመጠገንና የጉዳት ደረጃውን ለመመልከት ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣንና ከአማራ ክልል የመንገድ ፈንድ የሥራ ኃላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡
በአማራ ክልል ከሐይቅ ወደ ውጫሌ መግቢያ ያለን ድልድይ በስካፋተር ቆፍሮ ንዲወድም አድርጓል። ከወልዲያ ከፈረጠጠ በኋላም የአለዋ ድልድይን በከባድ መሳሪያና ፈንጅ በመታገዝ አውድሟል።