ስለዚህ ባለ ብዙ ጠበቃው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‘ሃገር ለማዳን የጦር ሜዳ ስለወረዱ በጥያቄ ብዛት አታድክሟቸው’ የሚለው ጥብቅና ሃገር ለማዳን ጦር ሜዳ ለወረዱት እነ ዘመነ ካሴም ሊሰራ ይገባል።
ጅንስ እና ሱፉን አውልቆ መለዮ ለብሶ የሚንጎራደደው ዲያስፖራም ሆነ ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛም ሆነ ካድሬ ይህን ሊናገር ይገባል! ካልሆነ መለዮ ያስለበሳቸው የመንግስት አዝማሪነት እንጅ ሌላ እንዳልሆነ ገሃድ ይወጣል።