የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው ድርጅት የምዝገባ ፈቃድ ተሰረዘ

November 26, 2021
የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው ድርጅት የምዝገባ ፈቃድ መሰረዙን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስታወቀ።
ድርጅቱ በአዋጅ 1113/2011 አንቀጽ 88/3 መሰረት ዳግም ተመዝግቦ በምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር 2936 ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል።
የአስቸኳይ ጊዜ መምሪያ ዕዝ የአገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም የሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ሲያምን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለሽብር ቡድኖች የሞራልም ሆነ የቁሳቁስ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ የሚጠረጥረውን የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ ሊያዝ ይችላል ተብሎ በተደነገገው መሰረት ከላይ በስም የተጠቀሰው ድርጅት ፈቃድ እንዲሰረዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ ዕዝ ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚሁ መሰረት የፍትሕ ሚኒስቴር የድርጅቱ ፈቃድ እንዲሰረዝ ለባለስልጣኑ በደብዳቤ አሳውቋል።
በዚሁ መሰረት የሰላምና ልማት ማዕከል የተባለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የምዝገባ ምስክር ወረቀት (ፈቃድ) ከዛሬ ጀምሮ የተሰረዘ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
ፈቃዱ የተሰረዘበት ድርጅት የኢትዮጵያን ህልውና አደጋ ላይ ከጣለው የአሸባሪው ህወሃት ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ መንግስት ላይ ሲያሴር የሚያሳይ የቪዲዮ ምስል ወጥቶ የድርጅቱ ገመና መጋለጡ ይታወቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ከዕዉነት ሽሽት…አስከ የት ? – ማላጂ

Next Story

“ካሳጊታ በመከላከያ ሰራዊት እጅ ገባች” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጦር ግንባር

Go toTop