![](https://cdn.statically.io/img/amharic.thehabesha.com/wp-content/uploads/2021/11/257132453_433477018346212_5192922119429294731_n.jpg?quality=100&f=auto)
እነሱ ሀገር ፈርሶም ቢሆን ዘርፈው ለመኖር ማንኛውንም ነገር ነገር ለማድረግ ያላቸውን እልህ ያህል እኛም ኢትዮጵያን ለመጠበቅና ሀገር ለማስቀጠል ቁርጠኝነት ሊኖረን ይገባል።
..እነኚህ ሰዎች በፍፁም ወደ ፖለቲካው አካባቢ ሊመጡ የሚቹሉበት መንገድ መኖር የለበትም፤ ምክንያቱም አገር ለማፍረስ እንጂ በምንም አይነት አገርን በጋራ ለመገንባት ፍላጎት አላቸው ብዬ አላምንም። የተሳሳተ ትንተና ቢኖረኝ እመኝ ነበር ነገር ግን እስከማቀው በህወሃት ላይ የተሳሳተ ትንተና አድርጌ አላቅም።
የትግራይ ሕዝብ የኛ ወገን ነው፤ ነገ ከዛ ሕዝብ ጋር የምንኖር እንደሆነ አውቀን ንፁሃን ሰዎችን ላለመጉዳት እየተጠነቀቅን ይሄን ጦርነት መጨረስ አለብን! የገባንበት ነገር ከህወሓት መሸነፍ ውጪ ሌላ መፍትሄ የለውም።
ትኩረታችን ህወሓት ላይ አድርገን ንፁሃንን እንዳንጎዳ ተጠንቅቀን ጦርነቱን ማጠናቀቅ ከቻልን የውጪ ሃይሎች የሚያመጡት ነገር የለም። ለውጪ ሃይሎች/ ጠላቶቻችን እየተመቻቸው ያለው የውስጣችን መተራመስ ነው።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ