ከሞት የማይሻል ዝምታ

February 1, 2014

በጠባቦች ፍልስፍና
በጭፍኖች ጉርምስና
በአጉራ ዘለሎች እርግጫ
በሳዲስቶች የግፍ ጡጫ
በራስ ወዳዶች በደል
እናት ሐገር ስትበደል
የእናት ሐገርን ስቃይ
ጣሯን
የእምዬን ምሬት
አሳሯን
ከሞት በማይሻል ዝምታ
ከሞት በማያስጥል ጉምጉምታ
ራሳችንን እጉልበታችን ስር ቀብረን
በእህህ የሆድ ዝማሬ
በውስጥ ዜማ ደንቁረን
ባለግዴታ ትከሻችን
በውዴታችን ሟሙቶብን
ባለብረት ሞራላችን
በእሳት እንደጭድ ላሽቆብን
ከእግር እስከራሳችን መክነን
እናድናት ዘንድ ቢሳነን
ይህቺ ምድር
የዓለም ብርሐን የነበረች
በሀያል ጨለማ አደረች
የሰው ሐገር የነበረች
በሰው ረሐብ አረረች።
እስክንድር ልሳነወርቅ
2006 ዓ/ ም

Previous Story

“የህዝብን የነጻነት ፍላጎት አፍኖ እስከ መጨረሻው መቆየት አይቻልም” – ሸንጎ

Next Story

ድርቅ ለመታው ፖለቲካ ማዳበሪያ፦

Go toTop