የሶማሌ ክልል ያላግባብ ገዳማይቱ ገዋኔ ለአፋር የተሰጠብኝን አስመልሳለሁ ብሎ መግለጫ አውጥትዋል አፋርም አይሞከርም እያለ ነው።
በአዋሽ ሸለቆ ለተመላለስን እነዚህ ትናንሽ መንደሮች በአፋር አስተዳደር ስር እንደነበሩ እናውቃለን ከዘመነ ወያኔ በፊት።
አሰብ አዲስ አበባ መንገድ በመሀል ስለሚያልፍባቸውም ትልቅ የኢኮኖሚ ጥቅም ይሰጣሉ ያገኛሉም። በሆቴል ነዳጅ ንግድ ሳቢያ።
ገዋኔ አካባቢ አዋሽ ወንዝን አቛርጠውየ ኢሣ ጎሳ የግጦሽ መሬት ፍለጋ በአፋርና ኢሳ መካከል ግጭት ተነስቶ ወታደር ሲነቃነቅ አይቼአለሁ።
ወያኔ አካባቢውን ለመቆጣጠር ከ ሻቢያ ጋር በመሆን የአፋር ነዋሪዎች ላይ ብዙ ጥቃት ፈፅሞ እስከ ባድሜ ጦርነት የበላይነቱን አሳይቶ ነበር።
የኦሮሞ ኢህአዺግ ከጅጅጋው የዛሬ ዐመት ፀረ አማራ ፀረ ክርስቲያን ግድያና ማፈናቀል በዃላ አብዲ ኢሌን አስሮ የሶማሌ ክልል በአፍቃሪ ኦሮሞ ኢህአዲግ አዺስ ተሾሚዎች ስር ነው። አፋር እስካሁን ለርሱ የቆሙ መሪዎች አላገኘም።
የሶማሌ ክልል ከኦሮሞ ጋርም ሰላም ዕርቅ መፈለጉን እየሰማን ባለበት ለምን ጦርነት ከአፋር ጋር አሁን ተፈለገ ??
ዋናው ምክንያት የአፋርን ህዝብ ከአሰብ አዲስ አበባ መንገድ ለማራቅ ነው።
ይህ አዲስ የሚፈጠረው ኦሮሞ ኢህአዲግ ሶማሌ ግንባር ወደፊት ከሚፈጠረው የሲዳማ ክልል ጋር በመሆን የኢኮኖሚ የበላይነት ለማፈርጠም የሚደረግ ዕንቅስቃሴ ነው።የጃዋር መሀመድ OMN ፊንፊፊኒ ዋና ከተማው አድርጎ።
ባለፈው አንድ ዐመት የኦሮሞን ክልል ለማስፋፋት የተደረጉት ማፈናቀሎች የሰሞኑ የቤኒሻንጉልን ጨምሮ ይሄን ግልፅ ያደርገዋል።
የአፋር ጥንታዊ ከተሞችን ለመውሰድ የሚደረገውን ትንኮሳ የማስቆም ሀላፊነት ያለበት ገዢው ሀይል ከሀላፊነት መሸሽ አይችልም።
የአፋር ህዝብ ና አማራ ላይ በወያኔ ኦነግ የተጀመረዉን 28 ዐመት ያስቆጠረው ሽብር መከላከል ኢትዮጵያን ማዳን ነው።