በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

February 20, 2019

በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=SvwytfrDZTg&t=73s

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚሰራጨው ሳምንታዊው በረራ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ እንደዘገበው ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አና ጎሜዝ የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ በምርጫ 97 የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት አና ጎሜዝ በወቅቱ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ እሳቸው ዘንድም ብዙ ማስረጃዎች እንዳሉ የተናገሩ ሲሆን አጠቃላይ የነበረው ሁኔታ በታሪክ ባለሙያዎች ተጠንቶና ተተንትኖ እንዲፃፍ ከታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር እንደተነጋገሩበት መግለፃቸውን ጋዜጣው አስረድቷል፡፡ አና ጎሜዝ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዱ ‹‹በእለቱ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሄጄ ነበር፡፡ ሆስፒታሉ ውስጥ በርካታ አስክሬንና ቁስለኛ አይቻለሁ፡፡ የህክምና ባለሙያዎች በእንባ እየተራጩ ነበር፡፡ ‹እየጨፈጨፉን ነው፣ አንድ ነገር አድርጉ› ይሉን ነበር›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ይህንን ሁኔታ እንደተመለከቱ ከዚያ ወጥተው በቀጥታ ወደበረከት ስምኦን ቢሮ እንዳመሩና ለበረከት ጉዳዩን ሲነግሩት ጭራሽ እናንተ ተጠያቂዎች ናችሁ እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡ ሲናገሩም ‹‹በወቅቱ ከበረከት ጋር ያደረኩት ንግግር በህይወቴ ከገጠሙኝ ሁሉ የተለየ ነበር›› ብለዋል፡፡ በምርጫ 97 ወቅት አውሮፓዊያን ንግድ ላይ በማተኮር አውሮፓ ከቆመላቸው እሴቶችና ከሰብአዊ መብቶች በተቃራኒ በመቆም ክህደት ፈፅመው እንደነበርም አውስተዋል፡፡ ላይ በጠ/ሚ/ር ዶክተር አብይ አህመድ አስተዳደር የተሻለ ነገር እንደሚታይ የገለፁት አና ጎሜዝ ይህ ለውጥ እንዲቀጥልና ወደመሬት ወርዶ ቀጣይነት እንዲኖረው ግን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን ማድረግና ለወጣቶች ስራ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ማስገንዘባቸውን ከበረራ ጋዜጣ አንብበናል፡

Previous Story

‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ ነው”

Next Story

የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን ተሰጠ

Go toTop