በቅርቡ ህይወታቸው ያለፈው የቀድሞው ፕሬዚደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ልጆች በአባቸው ስም ባሉ ፕሮጀክቶች ከመንግስት በስተቀር ማንም ግለሰብ ትርፍ እንዳያገኝ ከለከሉ፡፡
https://youtu.be/J8BZqY2t65c
ይህ ክልከላቸው ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ህጋዊ እርምጃ የሚወስዱ መሆኑን አራተኛ ልጃቸው የሆኑት አቶ ሰለሞን ግርማ አስጠንቅቀዋል፡፡ በ94 አመታቸው ያረፉት የቀድሞው ፕሬዚደንት የተለያዩ ፕሮጀክቶችንና ፋውንዴሽኖችን በስማቸው እንዲከፈት አድርገው የነበረ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በቡታጅራ ትምህርት ቤት ለመገንባት የታሰበ እቅድ ይገኝበታል፡፡ ይህ ፕሮጀክትም 129 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ለትምህርት ቤቱ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብም እንቅስቃሴ ተጀምሮ ነበር፡፡ ይህ ፕሮጀክት ምንም ህጋዊ መሰረት የሌለው እንደነበር ለሪፖርተር የተናገሩት አቶ ሰለሞን ግርማ ወደፊትም በፕሮጀክቱ ዙሪያ የሚደረገው እንቅስቃሴ ህጋዊ ካልሆነ እንዲቆም ጠይቀዋል፡፡ ሌሎች ፕሮጀክቶችም ካሉ ቤተሰቦቹ ሳያውቁ ምንም እንቅስቃሴ እንዳይደረግ አሳስበዋል፡፡