ሲኖዶሱ የፓትርያርኩን ውሳኔ አስቀየረ

October 25, 2013

ቅዱስ ሲኖዶሱ በትናንትናው የስብሰባ ውሎው ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ በአብላጫ ድምጽ ወስኖባቸው የነበሩት የአዲስ አበባው ሊቀ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ በዛሬው ዕለት ፓትርያርኩ አቡነ ማቲያስ ‹‹አዲስ አበባ የእኔ ልዩ ሐገረ ስብከት በመሆኑና ማንም ሊያዝበት ስለማይችል ሊቀ ጳጳሱ በቦታቸው እንዲቀጥሉ በመወሰን የትናንቱን ውሳኔ ሽሪያለሁ››ማለታቸውን ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ስብሰባው ከሰዓት በኋላ ቀጣዩን አጀንዳ በማንሳት ከመወያየቱ በፊት ተቃውሞ እንዳላቸው የገለጹ ጳጳሳት ፓትርያርኩ የሲኖዶሱን ውሳኔ በመሻር ሊቀ ጳጳሱን በመንበራቸው እንዲቀጥሉ ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን በመግለጽ የቤቱን ውሳኔ እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡
ፓትርያርኩም በመጨረሻ የሲኖዶሱን ውሳኔ የመጨረሻ በማድርግ መውሰዳቸውን በመግለጽ አቡነ እስጢፋኖስ በሲኖዶሱ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ሲኖዶሱ በነገ ውሎው በአቡነ እስጢፋኖስ ቦታ ሌላ ሊቀ ጳጳስ ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡ ፍኖተ ነፃነት

Previous Story

በአፍሪካ ውስጥ በቅዠት የሚባንኑት እነማን ይሆኑ ?

Next Story

የአንድነት አመራር አፈና እና ድብደባ ተፈጸመባቸው

Go toTop