(ዘ-ሐበሻ) ባህርዳር በተለምዶው አንዳሳ በሚባለው አካባቢ በተከሰተ ኮሌራ በርካታ ሰዎች መታመማቸው ተሰማ:: 15 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉም ምንጮች ተናግረዋል::
በባህርዳር አዲስ ዓለም ሆስፒታል ውስጥ የታመሙት ከ30 በላይ ሰዎች እየታከሙ መሆኑ ሲሰማ 15 ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል::
በባህርዳር ሕዝባዊ ተቃውሞ እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት እስካሁን ያልተከሰተው ኮሌራ አሁን ተከሰተ መባሉ ብዙዎችን እያነጋገረ ባለበት በዚህ ሰዓት ምናልባት ስርዓቱ በአማራው ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን ተቃውሞ አቅጣጫ ለማስቀየር ሆን ብሎ ያደረገው ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ::
በተለይ ይህ ኮሌራ በአንድ አካባቢ ብቻ ማለትም አንዳሳ በተባለው ቦታ ብቻ ተከሰተ መባሉ አነጋጋሪ ሲሆን ሆን ተብሎ ውሃን በመበከል የተደረገ እንዳይሆን የሚሉ ጥርጣሬዎች አለ:: በዚህም መሰረት ማንኛውም የባህርዳር ነዋሪ ውሃን አፍልቶ እንዲጠጣ ጥሪ ቀርቧል::
በተለይ በዚህ ሰሞን በሶሻል ሚድያዎች ስርዓቱ የትግራይ ተወላጆችን ከጎንደር እና ባህርዳር እያስወጣ ባለበት ወቅት አማራውን ለመመረዝ ሴራ እየተጎነጎነ ነው የሚሉ ወሬዎች ሲሰራጩ ነበር::