ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

August 13, 2013

ኢሳት ቴሌቪዥን

ኦህዴድ ኢሳትን ለማስቆም እንደሚሰራ አስታወቀ

ነሃሴ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በነቀምት ባደረጉት ስብሰባ ህዝቡ ኢሳትን እንዳይመለከት ካድሬዎች ከፍተኛ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
አመራሮቹ ኢሳት የአሸባሪ ድርጅቶች ንብረት በመሆኑ፣ ህብረተሰቡ ኢሳትን መመልከቱን እንዲያቆም ባለስልጣኖቹ ወትውተዋል።
በስብሰባው ወቅት ለካድሬዎች ከተነገራቸው ነገር መካከል አንዱ ኢሳትን በሚመለከት ህግ ሊወጣ ነው መባሉ ነው። ምን አይነት ህግ እንደሚወጣ ግን ባለስልጣኖቹ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
ኢሳት በናይልሳት የሚያሰራጨው ስርጭቱ በአፈና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ላለፉት 7ወራት በኤስ ኢ ኤስ 5 እና በአሞስ ላይ የቴሌቪዥን ስርጭቱን እንዲሁም በተለያዩ የሬዲዮ ሞገዶች የኢትዮጰን ህዝብ እያገለገለ ይገኛል።

Previous Story

አንድነት ፓርቲ ነሃሴ 5 ቀን 2005 ዓ.ም በመብራት ሃይል አዳራሽ ያደረገው ስብሰባ ከፊል ገፅታ አንድ

Next Story

Hiber Radio: በኢትዮ- ኬኒያ ድንበር ላይ ውጥረት ነግሷል

Go toTop