ጋዜጠኛ ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ሊሞሸር ነው * የሠርጉን ወጪ ሺህ አላሙዲ ችለዋል

September 3, 2015

(ዘ-ሐበሻ)ጋዜጠኛና ኮሜዲያን ሠይፉ ፋንታሁን እሁድ ጷግሜ 1 ቀን 2007 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ሊሞሸር ነው፡፡ የሰይፉ ሚዜዎች ድምፃዊ ታደለ ሮባ፤ አርቲስት ሚኪ(ባለታክሲው ፊልም ላይ የሚሰራው)፤ ጋዜጠኛ ታደለ አሰፋና ሌሎች ሁለት ጓደኞቹ መሆናቸውን ለመረዳት ችለናል፡፡

የሰርጉን ወጪ ሙሉ በሙሉ የሚሸፍኑት ሼህ መሐመድ አል አሙዲ ናቸው፡፡ በዚህ መሰረት ባለፈው ሳምንት ሠይፉ ከአርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ ጋር ወደ ዱባይ አምርቶ ለሰርጉ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ሸማምቶ ተመልሷል፡፡ በሼህ መሐመድ አል አሙዲ የተሰጣቸውን የ165 ሺ ድርሃም በመያዝ ወደዱባይ ያቀኑት ሰይፉና ሰራዊት የሚዜዎችን ልብስና ጫማ ጨምሮ በርካታ ሻንጣ ቁሳቁሶች ገዝተው እንደተመለሱ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልፀውልናል፡፡

Previous Story

የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው! (በፍቃዱ ኃይሉ)

Next Story

Hiber Radio: አሜሪካ ሶማሊያ ለሚገኘው የኢሕአዴግ እና የጅቡቲ ጦር የመረጃና የስለላ ስልጠና እየሰጠች መሆኗ ታወቀ – ሕንድ ከኢትዮጵያና ከኤርትራ ማንን እንደምመርጥ ተቸግሬያለሁ አለች (ሌሎችም ዜናዎች አሉ)

Go toTop