ኣሸጎዳ የንፋስ መብራት ማመንጫ ሃይል ዲናሞ በመቃጠሉ ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆነ

February 14, 2015

ከአምዶም ገብረሥላሴ

በመቐለ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኝ የኣሸጎዳ በንፋስ የሚሰራ ኤለክትሪክ ማመንጫ ሃይል በዲናሞ መቃጠል ምክንያት ከስራ ውጭ መሆኑ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ 150 ሜጋዋት የማመንጨት ኣቅም የነበረው ሲሆን ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በመቃጠሉ ሃይል የማመንጨት ኣቅሙ ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ ቅያሪ በሃገር ውስጥ እንደሌለና ከፈረንሳይ ሃገር እንደሚመጣ ታውቋል። የህወሓት የ40 ዓመት የልደት በዓል እንደ ታላቅ ውጤትና ማጣፈጫ ተደርጎ ሊወሰደ ታስቦ የነበረ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቁጣና ድንጋጤ መፍጠሩ ታውቋል።

የትግራይ ባለስልጣናት እንደ ግዝያዊ መፍትሄ ኣድርገው የወሰዱት የየካቲት በዓል እስኪያልፍ ከፈርንሳይ በክራይ እንዲመጣና ብልሸት እንዳልደረሰው ኣስመስሎ በማሳለፍ በዓሉ ከተጠናቀቀ በሗላ ዲናሞው ወደ ፈረንሳይ እንዲመለስ የሚል ትእዛዝ ኣስተላልፈዋል። የህወሓት ባለስልጣና የየካቲት በዓል ታዳሚዎች ኣሳፋሪ በሆነ ድራማ ኣጭበርብረው ለመመልስ ከፈረንሳይ ዲናሞ ተከራይተው ካሳዩሗቹ በሗላ ተመልሰው ወደ መጣበት ይመልሱታል።

ህወሓት የዲናሞው መቃጠል ለየካቲት በዓል ማክበርያ ካወጣችው 1 ቢልዮን ብር ወጪ የምታወጣው ተጨማሪ ግዙፍ ብር ይሆናል።

Previous Story

በትዳርሽ ላይ የምትፈጽሚያቸው 5 ታላላቅ ስህተቶች (በተለይ ሴቶች እንዲያነቡት የተዘጋጀ)

Next Story

ሰማያዊ ለአንድነት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሊያደርግ ነው

Go toTop