አቶ ሙሼ ሰሙ ከኢዴፓ አባልነታቸው ለቀቁ

August 15, 2014

ከዳዊት ሰለሞን

ከአቶ ልደቱ አያሌው ጋር በመሆን ፓርቲው ከተመሰረተበት 1992 ጀምሮ በህዝብ ግኑኝነት፣ በጸሀፊነትና በፕሬዘዳንትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ ከሁለት ሳምንት በፊት ለፓርቲው ጽ/ቤት ባስገቡት ባለ ሶስት መስመር ደብዳቤ ከፓርቲው የማእከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸውና ከተራ አባልነት ጭምር ኢዴፓን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ሙሼ ለ14 ዓመት ያህል የተጓዙበትን ፓርቲ ለመልቀቅ የወሰኑት በምን ምክንያት እንደሆነ በደብዳቤያቸው ያልገለጹ በመሆኑ የፓርቲው አመራሮች ምክንያቱን ለመግለጽ መቸገራቸውን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ ደብዳቤውን ስለማስገባታቸው በስልክ የተጠየቁት ሙሼ ‹‹በራሴ መንገድ ምክንያቴን ይፋ አድርጋለሁ››ብለዋል፡፡

ሙሼ ኢዴፓን ለመጨረሻ ግዜ ያገለገሉት በፕሬዘዳንትነት ሲሆን አንድ ተርም ብቻ በቦታው ካገለገሉ በኋላ በድጋሚ የመመረጥ ዕድል እያላቸው በፈቃዳቸው ራሳቸውን ከዕጩነት ማግለላቸው አባላቱን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡

Previous Story

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ

Next Story

በሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች የተጀመረው እስር ተጠናቅሮ ቀጥሏል

Go toTop