በምስራቅ ጎጃም የመኢአድ አባል በካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አለፈ

June 20, 2014

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው በምስራቅ ጎጃም በነማይ ወረዳ ደንጎሊማ ቀበሌ አቶ ሞሳ አዳነ የተባሉ የመኢአድ አባል ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን ከቤታቸው ወደ እስር ቤት መሄድ አለብህ በሚሉ የብአዴን ካድሬዎች ድብደባ ሕይወታቸው አልፏል፡፡

ይህን ድርጊት የፈጸሙት ሁለት የብአዴን ካድሬዎች አቶ አዲሱ ጫኔና አቶ ብርሃኑ ታመነ ወደ መኖሪያቸው በመሄድ ወደ እስር ቤት ትሄዳህ በማለት ለማስገደድ ሲሞክሩ በተፈጠረ እሰጣገባ አቶ ሞሳ አዳነ ካድሬዎቹ በፈጸሙባቸው ከፍተኛ ድብደባ ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡ በተያያዘ ዜና በዚያው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የመኢአድ አባል አቶ ይበልጣል ወንድሜነህ ቤትህ መሣሪያ አለ በሚል ጥርጣሬ እያሳደዱዋቸው እንደሚገኙና እሳቸውም አካባቢያቸውን ጥለው እንደሸሹ የመኢአድ የሕ/ግንኙነት ኃላፊ ለፍኖተ ነፃነት ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል፡፡

Previous Story

በሃዋሳ 3 የአንድነት አመራርና አባላት ታሰሩ – “እስሩ ቅስቀሳውን አያስተጓጉለውም”

Next Story

የትግራይን መስቀል ስለመሸከም (ተመስገን ደሳለኝ)

Go toTop