በግንደ በረት በተማሪዎች እና በክልሉ ፖሊስ መካከል ከፍተኛ የሆነ ግጭት ተከሰተ

June 13, 2014

በምእራብ ሸዋ ዞን በኦሮሚያ ክልል በግንደበረት ወረዳ በተማሪዎች እና በወያኔ የፖሊስ ሃይሎች መካከል በተከሰተ ግጭት አንድ ተማሪ ሞቶ አራት መቁሰላቸውን የአከባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

ከትላንትና ጀምሮ ሲንከባለል የመጣው ግጭት ከዚህ ቀደም በኦሮምያ ክልል ውስጥ ከተነሱ የተማሪዎች አመጽ ጋር ተያያዥነት ያለው እና ጥያቂውም የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እና የሞቱ የኦሮሞ ተማሪዎች ጋር የተያያዘ ሲሆን ዛሬ በቀጠለው ተቃውሞ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች እና የወረዳው ነዋሪ በጋራ ሰልፍ በመውጣት ቁጣቸውን የገለጹ ሲሆን አስተዳደሩ ድረስ በመሄድ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የፌዴራል ፖሊስ በመምጣት የበተናቸው ቢሆንም ቀኑን ሙሉ በከተማው ከባድ ረብሻ እንደነበር እና ከቆሰሉ ተማሪዎቹም አንዱ መሞቱን የወረዳው ነዋሪዎች ተናግረዋል ሲሉ ምንጮቹ ጠቁመዋል።

በነገው እለት የ12ኛ ክፍል መሰናዶ ፈትና ከወሰደ በኋላ የተገደለውን ተማሪ ለመቅበር ይወጣል የተባለው ሕዝብ ተቃውሞ እንዳያሰማ የወረዳው እና የከተማው ባለስልጣናት በመስጋት ፖሊሶች ያሰፈሩ ሲሆን ሕዝቡ ቁጣው እንዳልበረደ እና በስፋት ተቃውሞው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

Previous Story

የመሬት ወረራን በመቃወሜ የተፈፀመብኝ በደል – አበበ ሆንጃ (ከሰበታ)

Next Story

በሪያድ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በገንዘብ እጥረት 3000 ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው * ወላጆች ለልጆቻቸው መበተን ዲፕሎማቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ

Go toTop