Español

The title is "Le Bon Usage".

የአማራን የህልውና አደጋ ከመከላከል ትግል ጋር የተያያዙ የተመጠኑ የግል ምልከታዎች!

ቀን የካቲት 2017
በአንዳርጋቸው ጽጌ

ክፍል ፡ 7 ህብረ ብሄራዊ የሆነው የጸረ ወያኔ ትግል እና አዲሶቹ የአማራ ብሄረተኞች

አማራ የተሳተፈባቸው በወያኔ ዘመን ከስርአቱ ጋር የተደረጉ ትግሎች በሙሉ፣ አማራው በዋንኛነት በህብረ ብሄራዊ ወይም ሃገራዊ ድርጅቶች ውስጥ የተሳተፈባቸው ናቸው። በዋነኛነት ያልኩት ያለምክንያት አይደለም። በአማራነት ተደራጅቻለሁ ሲል የነበረው ብአዴን የወያኔ ተላላኪ ስለነበር በአማራነት ከተደራጁት መሃልም ሊቆጠር አይችልም። ኢህዴን በወያኔ ትእዛዝ ወደ ብአዴን ከመቀየሩ በፊት ለአማራ ህዝብ መብት መከበር ለመጀመሪያ ጊዜ በአማራ ስም የተቋቋመው ድርጅት የመላው አማራ ህዝብ አንድነት ድርጅት ነበር (መአህድ)።

በሌላ ጽሁፍ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ይህ ድርጅት “አማራ” የሚል ስያሜ ይሰጠው እንጂ፣ በማንነቱ መሰባሰቢያ ላጣው ኢትዮጵያዊ ለሆነው ሁሉ መሰባሰቢያ ተደርጎ ነበር የተወሰደው። መአህድ ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ከአማርኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ የማይናገሩ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በብሄር በመደራጀቱ፣ ኤርትራ የሚባል ብሄር በኢትዮጵያ ባላመገኘቱ መግቢያ ያጡ ከኤርትራውያን ቤተሰቦች የተወለዱ ኢትዮጵያውያንን ሳይቀር ያቀፈ ድርጅት ነበር። ሌሎችንም “ዘውግ ዘለል ማንነት አለን፣ ነገር ግን ዘውግ ዘለል የሆነ ወያኔን የሚቃወም የፖለቲካ ድርጅት ማግኝት አልቻልንም” ያሉ ኢትዮጵያወያንም በመላው አማራ ህዝብ ድርርጅት ውስጥ ገብተው ነበር።

የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት “በስም አማራ በይዘት ግን ኢትዮጵያዊ ድርጅት ነበር” ማለት ብዙ ማጋነን አይሆንም። ውሎ አድሮም የመላውን አማራ ህዝብ ድርጅት ወደ መላው ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ድርጅት እንዲቀየር ያደረገው ግፊት የመነጨው ይህን የመሰለው የአደረጃጀት ንድፈሃሳባዊ ጥራት አለመኖር ነው።

መላው አማራ፣ መላው ኢትዮጵያ ከሆነ በኋላም መላው አማራ የሚለውን ስም ይዞ የቀጠለ ድርጅት ነበር። መላው አማራ ብሎ የቀረው ድርጅት በሰው ሃይሉም በድርጅታዊ ጥንካሬውም አነስተኛ በመሆኑ በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ጥላ ተሸፍኖ እድገት ሳያሳይ የቀረ ድርጅት ነው። ዛሬም አለ። መላው አማራ ራሱን ወደ መላው ኢትዮጵያ ከቀየረ በኋላ “አማራን አሰባስባለሁ” የሚል ሌላ ድርጅት ሳይፈጠር በርካታ አመታት አልፈዋል። ከዛ ዘመን በኋላ ሌላው ትልቅ ተደማጭነት ያገኘው ድርጅት (አብን) አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ነበር። አብን ወያኔን በመጣሉ ስራ ላይ ምንም አስተዋጽኦ ያልነበረው፣ ወያኔ ሊወድቅ ቀናት ሲቀሩት በወጣት የአማራ ምሁራን የተፈጠረ ድርጅት ነበር።

በወያኔ ዘመን በአማራ ስም የተደራጁትን ድርጅቶች ደካማነት ካጤንን፣ አማራው በዋነኛነት ጸረ ወያኔ ትግል ያደረገው በሃገራዊ ፓርቲዎች ውስጥ በመሳተፍ እንደሆነ እንረዳለን። መላው ኢትዮጵያ፣ ኢዴፓ፣ በኋላም ቅንጅት ሊመሰረት አካባቢ የመጣው ቀስተ ዳመና፣ ቅንጅት ከተበተነ በኋላ በአንድነት ፓርቲ፣ በሰማያዊ ፓርቲ፣ በመጨረሻም መሰረቱ በአብዛኛው በውጭና በጎረቤት ሃገራት ቢሆንም በአርበኞች ግንቦት ሰባት ውስጥ ነው።

በኤርትራ ምድር በርካታ በብሄር የተደራጁ ድርጅቶች ቢኖሩም በአማራነት የተደራጀ ድርጅት የመጣው ከሁሉም ዘግይቶ ነው። የአማራ ህዝባዊ ሃይል የሚባለው በኮነኔል አለሁበል አማረ የተመሰረተው ድርጅት ነው ። ይህም ድርጅት ሌሎች ሃገራዊ ድርጅቶች ማድረግ እንደሚችሉት ብዙ አማሮችን ማሰባሰብ አልቻለም። ከዚህ ውጭ በኤርትራ ውስጥ ከሁሉም ትልቁ የሆነው የአማሮች መሰባቢያ የነበረውና በአብዛኛው በጎንደር አማሮች የተሞላው ድርጅት በአማራ ስም ሳይሆን የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር በሚል ስያሜ የሚታወቅ ነበር።

ለረጅም ዘመን አማራን በአማራነት ለማደራጀት ከሚደረግ ጥረት ይልቅ በሃገራዊ ድርጅቶች ውስጥ እንዲሰባስብ ማድረግ ቀላል የሆነበት ምክንያት፣ አማራው በአማራነት ራሱን ለይቶ እንዲያደርጅ የሚያደርግ ምክንያት ስላጣ፣ በአማራነት ተለይቶ በደል እንደሚደርስበትና እንደሚጠቃ ስላልተገንዘበ ወይም ስላልተሰማው አልነበረም። የዘመኑ የአማራ ብሄረተኞች ሊያሳምኑን እንደሚጥሩት በህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ወስጥ ሲሳተፉ የነበሩ አማሮች ይህ የአማራ ስቃይ የማይረዱና የማይሰማቸው ስለነበሩ አልነበረም። ለእነዚህ አማሮች የአማራው መበደል መገፋት መሳደድ መገደል የመነጨው ወያኔ በሃገሪቱ ላይ የጫነው አማራው ያልተሳተፈበት፣ በዘር ላይ የተመሰረተ ህገ መንግስት፣ በዘር ላይ የተመሰረተ መንግስታዊና አስተዳደራዊ መዋቅር ነው ብለው ማመናቸው ነው። ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ይህን የወያኔን እኩይ ድርጊት ዋንኛዎቹ ተቃዋሚዎች ነበሩ።

ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ይህን የወያኔ በዘር ላይ የመሰረተ መንግስታዊ ስርአት ተቃውመው መቆማቸው አማራውን የሚስበው ጉዳይ ነበር። “እነዚህ ሃገራዊ ድርጅቶች ሲያሸንፉ ዘርን መሰረት ያደረገውን ፖለቲካ ኢኮኖሚ አስተዳደር ወዘተ ሁሉም ያከትምለታል፤ የአማራም መከራ ያበቃል” ከሚል እሳቤ ነው አማራውን በስፋት የህብረ ብሄራው ድርጅቶች ደጋፊና አባል የሆነው። “በወያኔ ዘመን በሃገሪቱ የተዘረጋው ዘረኛ ስርአት በማክትሙ በቅድሚያ እፎይታ የሚያገኝው ማህበረሰብ አማራው ነው” የሚል ስሌት ለብዙ አመታታ አማራው ከሃገራዊ ድርጅቶች ጋር ተቆራኝቶ እንዲቀጥል አድርጎታል።

ሌላው አማራው በሃገራዊ ድርጅቶች ውስጥ እንዲቀጥል ያደረገው ምክንያት ለሌሎች ሃላፊነት ከመውሰድ የመጣ ነው። “በአማራነት ተለይቶ መደራጀት፣ በብሄር መደራጀት የማይፈልጉ የተለያዩ ብሄር ተወላጆችን እና አንድ ወጥ ማንነት የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ያለአሰባሳቢ እንዲቀሩ ያደርጋል” የሚል ስጋት አማራውን ለረጅም ጊዜ ከሃገራዊ አደረጃጃት እንዳይርቅ ያደረገው ምክንያት ነበር። ኢትዮጵያ ለሚል ነገር አማራው ያለው ስሜትና ቀናኢነትም የራሱ ደርሻ እንደሚኖረው አይካድም።

ዋናው በሃገራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ አማራው በስፋት የሚሳተፍበት የፖለቲካ ምክንያት ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች እውነተኛ የሆነ በዜግነት ላይ የቆመ ህብረ ብሄራዊ አገር ይፈጣርሉ ብሎ ማሰቡ ነው። የህበረ ብሄራዊ ድርጅቶችም የፖለቲካ ፕሮግራም ይህን የአማራውን ፍላጎት የሚያንጸባርቅ ነበር። በመሆኑም የአማራ በደል፣ መከራ የሚሰማው አማራ በስፋት በህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ የተሳተፈው ረቂቅ የሆነ የራሱን በደልና መከራ የሚያስረሳ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር ሳይሆን የአማራ ችግር ኢትዮጵያዊ በሆነ የፖለቲካ እሳቤና አደረጃጀት ሊፈታ ከቻለ ለምን እኔ ሌላ በብሄር የተደራጀ ድርጅት ፈጥሬ ሁኔታዎችን አወሳስባለሁ ከሚል እሳቤ መሆኑ መታወቅ አለበት። ሃቁ አማራው “በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ማውረድ ይቻላል” ፤ በህብረ ብሄራዊ አደረጃጀት የአማራንም ጉዳት፣ የኢትዮጵያንም ጥፋት ማስቆም ይቻላል ብል ማመኑ ነው። ስለዚህ የትኛውም አማራ በህብረ ብሄራዊ ድርጅት ውስጥ የሚያደረገው ትግል የአማራን መከራ ለማሳጠር የሚደረግ ትግል አካል ነበር ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል። በቅንጅትም ይህን በሌሎች ፓርቲዎች ውስጥ፣ በኋላም በአርበኞች ግንቦት ሰባት ውስጥ በስፋት የተሰባስበው አማራ ይህ አይነት የአማራ ንቃተ ህሊና የነበረው ነው።

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን የአማራ ብሄረተኞች አድርገው የሚያቀርቡ አካላት፣ ቀደም ብሎ በህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች በተለይ ደግሞ እንደ ግንቦት 7 የመሳሰሉ ድርጅቶች ውስጥ ሲታገሉ የነበሩ አማሮችን በጸረ አማራነት ሲከሱ ይደመጣሉ። እንዲህ አይነቱ ክስ ከላይ ባሰቀመጥኳቸው ምክንያቶች የተነሳ መሰረት የሌለው ክስ ነው። ይህን የምለው ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ ሲሳተፍ የቆየው፣ ገንዘቡን እውቀቱን ህይወቱን ሳይቀር የለገሰው አማራ በዋንኛነት የሚታገለው ለአማራ ስለነበር ነው። በወያኔ ስርአት በማንነቱ ተለይቶ ከአማራው በላይ ሌላ ማን ጉዳት ደረሰበት? ወያኔን ከመታገል በላይ ለአማራነት መቆም ከየት ሊመጣ ነው?

የወያኔ መሸነፍ የአማራ ድል ተደርጎ የሚታይበት ሁኔታም ከዚህ የመነጨ ነው። በተጨባጭ የማውቀው በኤርትራ ምድር የግንቦት ሰራዊት አባል ለመሆን የሚመጣው ወጣት 99.9 ከመቶ አማራ ነበር። ወደ ኤርትራ የሚገፋው “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ችግር ላይ ወድቃለች” የሚል ለኢትዮጵያ ከሚሰጥ ሃዘኔታ አልነበረም። በቀጥታ ከአማራ ህዝብ ስቃይና መከራ ጋር በተያያዘ ቁጭት ነበር።

እዚሁ ላይ ተጠቅሶ ማታለፍ ያለበት ጉዳይም አለ። የአማራ ህዝብ ሆነ ልሂቁ፣ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲወጣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ከፋፋይ ትርክትን በተመለከተ ሌሎችንም ጸረ ወያኔ ንግግሮቹን አዳምጦ ከየትኛውም ህዝብና ከየትኛው ልሂቅ ይበልጥ ድጋፉን የሰጠው፣ ወያኔ የዘረጋው፣ ለአማራ መገፋት፤ መበደል፣ መዋረድ፣ መፈናቀልና መገደል ምክንያት የሆነው የፖለቲካ ስርአት “አብይ አህመድ በሚወስዳቸው ርምጃዎች ፍጻሜውን ያገኛል” ብሎ ነው። ያለበለዚያማ አብይ አህመድን የት አውቆት ነው ድጋፍ የሚሰጠው። ዛሬ ወያኔዎችና ደጋፊዎቻቸው በሚድያ ሰራዊቶቻቸው እንደሚያቀርቡት አማራው ለአብይ የሰጠው ድጋፍ የትግራይን ህዝብ እንዲጨፈጭፍ ሳይሆን ወያኔ የዘረጋውን ጸረ አማራ መንግስታዊ ስርአት እንዲቀብርለት ነበር።

ወያኔዎች ከአብይ ጋር ግጭት ውስጥ ሲገቡም የአማራ ህዝብና ልሂቅ ከአብይ ጎን የቆመው ወያኔዎች በትግራይ ውስጥ ራሳቸውን በራሳቸው በማስተዳደራቸው፣ አዲስ አበባን ለቀው መቀሌ ላይ በመከማቸታቸው፣ ከማእከላዊ መንግስት ጋር ምንም ግኙነት የለንም በማለታቸው፣ አብይ የሚቃወመውን ምርጫ በማካሄዳቸው አይደለም። ጠዋት ማታ በኢትዮጵያ የዘረጉትን ለ27 አመታት አማራን አሳሩን ያሳየውን መንግስታዊ ስርአት ፍትሃዊና ሊቀጥል ይገባዋል ብለው የሚያስቡ፣ ይህንን ለማድረግ “የፌደራሊስት ሃይሎች” የሚል አማራውን በጠላትነት የሚያዩ አካላትን መቀሌ ላይ እያሰባሰቡ ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም በቂ ወታደራዊ ሃይል እንዳላቸው የሚያሳዩ ወታደራዊ ሰልፎች ትርእቶች ቀረርቶዎች ጋዜጣዊ መግለጫዎች መስጠታቸው ነበር።

“የሰሜን እዝ ላይ መብረቃዊ እርምጃ ወስደናል” የሚል መግለጫ በመስጠት ጦርነት ሲጀምሩ አማራውን መብረቅ የመታው “አብይ አህመድ ሊያስወግደው ይችላል” ብሎ ያሰበውን ዘረኛ ስርአት ወያኔዎች አብይን አስወግደው ሊያስቀጥሉት ነው የሚል ስጋት ነው። ይህ የሆነው አብይ ከወያኔ በላይ ዘረኛ ብቻ ሳይሆን መርዘኛ መሆኑን የአማራ ህዝብ ባልተረዳበት ሰአት ነበር። ወያኔ ያኔ የከፈተው ጦርነት፣ እንደ ዛሬው የአብይ አህመድ ጭንብል ተገፎ እውነተኛ ማንነቱ በሚታይበት ሁኔታ ቢሆን ኖሮ፣ የአማራ ህዝብ ለትግራይ መከላከያ ሃይል መንገድ እየጠረገ ምግብ እየሰጠ አዲስ አበባ ያደርሰው ነበር። ይህ የሚያሳየው አማራው ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውንም ማህበረሰብ በጥላቻና በጠላትነት የማያይ፣ ሰዎችን እና ቡድኖችን በድርጊታቸው የሚመዝን መሆኑን ነው።

ዛሬ አማራው ከአብይ አህመድ ጋርም የሚፋለመው አብይ ኦሮሞ ስለሆነ አይደለም። ኦሮሞ ስለሆነ ነው ብለው ሊያስምኑን የሚሞክሩ አሉ። ለእነዚህን አካላት፣ “አብይ ኦሮሞ መሆኑን እያወቀ ከማንም በላይ የደገፈው አማራ መሆኑን የሚያሳየውን ታሪካዊ ሃቅ በማመላከት ዝም ማሰኘት ይቻላል።

በህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ወስጥ በመሰባሰብ 27 አመት ሙሉ፣ ደከመኝ ስለቸኝ ሳይል ክወያኔ ጋር የታገሉ፣ በትግሉም ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈሉ አማሮች በድርጊታቸው፣ ከትግል ርቆ ከኖረው አማራ ይልቅ ሊኮሩ ይገባል።እነዚህ የአማራ ልጆች ለመተቸትና ለመንቀፍ የሚፈልጉ አካላት መመለስ ያለባቸው በርካታ ጥያቄዎች አሉ። ለመሆኑ የአማራ አበሳ የጀመረው ወያኔ ስልጣን ላይ እንደወጣ አይደለምን? ወያኔ ስልጣን ላይ በቆየባቸው 27 አመታት ውስጥ ወያኔን ለመታገል ምን አደረጋችሁ? የትኛውን ድርጅት አደራጃችሁ? የትኛውን የአማራ ማህበረሰብ አንቀስቃቀሳችሁ? የአማራ መገፋት መዋረድ መሰቃየት የተከሰተላችሁ ወያኔ ሊወድቅ ሲል ነወይ? እነዚህ አካላት ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

በጣም ወጣት የሆኑ የአማራ ብሄረተኞች ወያኔን ለምን አልተቃወማችሁም፣ አልታገላችሁም የሚል ጥያቄ ሊቀርብባቸው አይችልም ይሆናል። እድሜያቸው ከሰላሳ አምስትና ከዛ በላይ የሆኑና፣ በሃገራዊ ፓርቲዎች ውስጥ ወያኔን ሲታገሉ የነበሩ አማሮችን የሚኮንኑ ሰዎች ግን ወያኔ ያንን ሁሉ ዘመን አማራን ሲረግጥ ምንም ሲሰሩ ነበር? ህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ ካልነበራቸሁ የት ነበራችሁ? የሚል ጥያቄ ሊነሳባቸው የሚገባ ነው። እኔ በግሌ የሃገር ቤቱንም ሆነ የውጭ ሃገሩን ፖለቲካ የማውቀው ሰው ዛሬ የአማራ ብሄረተኛ ነኝ፣ ሌላው ሁሉ ከፊቴ ይጥፋ የሚል የአማራ ምሁር፣ አብዛኛው አማራው ሲረገጥ ሰጥ ብሎ ትምህርቱን ሲማር፣ ትምህርቱን ጨርሶ ስራ ሲይዝ፣ ስራ ይዞ ቤት ንበረት ሲያደላድል የኖረ እንደሆነ አውቃለሁ። አንዳንዱም በወያኔ አፋኝ መንግስታዊ ስርአት ውስጥ ትምህርትና ስልጠና ወስዶ ከወያኔ ጋር በሞዳሞድ ስራ ተሰጥቶት ሲሰራ የነበረ ነው።

አንዳንዱ የዘመኑ የአማራ ብሄረተኛ፣ በህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ውስጥ ሲታገሉ የነበሩ አማሮችን ለመናገር የሞራል ድፍረቱን ከየት እንዳመጣው አላውቅም። እንዲህ አይነቱ ፍጥረት ወያኔ የአማራን ህዝብ መጨቆኛ ዋናው ክንድ አድርጎ ባቆመው ብአዴን ውስጥ በዋና ካድሬነት ሲሰራ የነበረ ነው። በውጭ ሃገርም ቢሆን አንድ ቀን ለጸረ ወያኔ ትግሉ ገንዝብ፣ እውቅተ፣ ጉልበት ያላዋጣ በየትኛውም ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቶ የማያወቅ ፍጥረት ድንገት ብቅ ብሎ “ዘራፍ ከኔ በላይ ለአማራ” ሲል እንሰማዋለን። ለአማራ ህዝብ የሚቆረቆር ማንኛውም ሰው፣ እነዚህ በከፋፋይ ቆሻሻ ድርጊቶቻቸው አማራን የሚከፋፍሉና አማራው ጠላቶቹን ረስቶ በውስጥ ሽኩታ እንዲጠመድ አጀንድ የሚፈጥሩ ግልሰቦችና ቡድኖች በቃችሁ ሊላቸው ይገባል። ከሌሎች እንማር፣ የራሳችንን ቆሻሻ ላውንደሪ በአደባባይ ማጠቡ ለጠላቶቻችን ፌሸታ ለወገን መከፋት ያስከትላል። ጉዳዩ በአማራ የህልውና ትግል ላይ ጉዳት የማያመጣ ቢሆን ኖሮ፣ በአማራ ስም አማራን ሲከፋፍሉ የሚውሉ አካላት ነውር በአደባባይ በማቅረብ በህዝብ ፊት ቀና ብለው እንዳይሄዱ ማድረግ ይቻል ነበር። ትግሉ ለግል ስምና ክብር ሲባል ያዙኝ ልቀቁኝ የማይባልበት፣ ከነድክመታችንና ጥንካሬያችን ሁላችንም የምናስፈልግበት፣ በአንድነት ከመቆም ውጭ ግዙፍ ጠላቶቻንን ማሸነፍ እንደማንችል ግልጽ የሆነበት ስለሆነ ሁላችንም ህሊናችንን በመፈተሽ አደብ እንድንገዛ ያስፈልጋል።

አሁን ባለንበት ወቅት በአማራ ክልል በሚደረገው ትግል ውስጥ ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የቀድሞ የግንቦት ሰባት የሰራዊት አመራራ የነበሩ ተዋጊዎች የሚመሯቸው የፋኖ ብርጌዶች ክፍለጦሮች አሉ። እነዚህ ተዋጊዎች በአራቱም የአማራ ክፍለሃገሮች ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በውጊያ ላይ የህይወት መስዋእትነት የከፈሉ የቀድሞ የግንቦት 7 ሰራዊት የነበሩ የፋኖ መሪዎችም አሉ። የአማራ ብሄረተኛነት በከፍተኛ ድረጃ አቆጥቁጦ አማራ የህልውና አደጋውን መመከት እንዲችል የፖለቲክ መነቃቃትን የፖለቲካ ሃላፊነት የወሰዱ ወሳኝ ሰዎች የቀድሞ ግንቦት 7 አባላት የነበሩ ናቸው። ይህ የሚያሳየው ሁኔታዎች በሚቀየሩበትና በሃገራዊ ፓርቲዎች አማካይነት የአማራ ችግር ሊፈታ አይችልም ተብሎ በሚያስበበት ወቅት ወጣቱ የአማራ ትውልድ፣ ከህብረ ብሄራዊ ድርጅቶች ወጥቶ በአማራነት ለመታገል ምን አይነት ብዥታ የሌለው መሆኑ ነው።

በውጭ ሃገራትም በስፋት በሚታየው የአማራ አደረጃጀት ውስጥ ቀደም ብለው የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባላት የነበሩ በርካታ ሰዎች ይገኙበታል። እንዲህም ሆኖ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውንና እውቀታቸውን በመስጠት የመስዋትነት አርአያ የሆኑትን በአማራነታቸው ከፍተኛ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ያላቸውን የቀድሞ የግንቦት ሰባት አባላት ከዳይስፖራው የአማራ ትግል ለማግለል የሚደረገው ጥረት እውን በአማሮች የሚሰራ ነወይ የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ ሆኖ አግኝቸዋሁ። የእነዚህን አማሮች ሁለንተናዊ ጥንካሬ ለምናውቅ ሰዎች “ይህ ድርጊት የአማራን ህዝብ ብቃት ያላቸውን ልጆቹን እንዳይጠቀም ጸረ አማራ ሃይሎች የሚሰሩ ሴራ ነው” ከሚል መደምደሚያ ላይ አድርሶናል። ይህ “አማራን ከዚህ በፊት በተለያዩ እንደ ኢህአፓ፣ ብአዴን፣ ግንቦት 7፣ ኢዴፓ፣ ቅንጅት፣ አንደነት፣ ሰማያዊ ፓርቲና ወዘተ አባላት ሆናችሁ ሰርታችኋል በሚል ስንኩል ምክንያት ለመከፋፈል የሚደረግ ጥረት የአማራውን የፖለቲካ ልሂቅ ካፒታል ለማመናመን ሆን ተብሎ የሚስራ የጠላት ሴራ መሆኑ ሁሉም አማራ በጥሞና ሊከታተለው፣ በዚህ መንገድ የሚሄዱ ከፋፋይ ግልሰቦችን እና ቡድኖችን ሊያስቆማቸው ይገባል።

አጋሩ!

Previous Story

የአማራ ክልል መንግስት ተኩስ አቁሜአለሁ ብሎ በማወጅ የመጀመሪያውን እርምጃ እንዲወስድ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጠየቀ

Latest from Same Tags

Zehabesha | Ethiopian Latest News, Top Analysis & Best Articles <h1 style="text-align:center">tHE HABESHA Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win</h1><title> <title><h2 style="text-align:left">Get the Best Scholarly Articles and Analysis on ZeHabesha</h2><title> <title><h3 style="text-align:right">Zehabesha Ethiopian News</h3><title> <title><h4 style="text-align:justify">Ethiopian Lates News</h4><title> <meta name="keywords" content="Ethiopian News, Ethiopia News, Ethiopian News Today, Top Stories, The Habesha, Latest News, Ethiopia, Breaking News, zehabesha, zehabesha Amharic News, The Habesha News, Headlines, borkena. bbc amharic, repoter, mereja, Ethiopian News provider"> <!-- Google Tag Manager --> <script>(function(w,d,s,l,i){w[l]=w[l]||[];w[l].push({'gtm.start': new Date().getTime(),event:'gtm.js'});var f=d.getElementsByTagName(s)[0], j=d.createElement(s),dl=l!='dataLayer'?'&l='+l:'';j.async=true;j.src= 'https://www.googletagmanager.com/gtm.js?id='+i+dl;f.parentNode.insertBefore(j,f); })(window,document,'script','dataLayer','GTM-5WDL6STX');</script> <!-- End Google Tag Manager --> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=G-W9E3TWE2TL"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'G-W9E3TWE2TL'); </script> <meta name="msvalidate.01" content="4781C31A916C7AB883D8AF1F4F3BFC49" /> <link rel="icon" href="/path/to/favicon.ico"> <link rel="icon" type="image/png" href="/thehabesha.com/favicon-96x96.png" sizes="96x96" /> <link rel="icon" type="image/svg+xml" href="/thehabesha.com/favicon.svg" /> <link rel="shortcut icon" href="/thehabesha.com/favicon.ico" /> <link rel="apple-touch-icon" sizes="180x180" href="/thehabesha.com/apple-touch-icon.png" /> <link rel="manifest" href="/thehabesha.com/site.webmanifest" /> <meta name="seobility" content="48b995a16caf3ab9d546a000c18b65d3"> <main> <!-- Main content of your page goes here --> </main> <script type="text/javascript" src="//cdn.rlets.com/capture_configs/d2b/aac/e54/1fc4f7ea32cf1e1d818a0f2.js" async="async"></script> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=TAG_ID"></script> <script src="https://www.googleoptimize.com/optimize.js?id=OPT-M8Z33GL"></script> <meta name="google-site-verification" content="Lf_65x5pXGn-W1TA8CsfJi-53aAyIKdfVyM_QkwpvgY" /> <head> <title>Ethiopian Latest News: Top Analysis and the best Articles<title> <script defer data-domain="thehabesha.com/mEUHSv" src="https://api.publytics.net/js/script.manual.min.js"></script> <script> window.publytics = window.publytics || function() { (window.publytics.q = window.publytics.q || []).push(arguments) }; publytics('pageview'); </script> <!-- Google tag (gtag.js) --> <script async src="https://www.googletagmanager.com/gtag/js?id=UA-215686007-9"></script> <script> window.dataLayer = window.dataLayer || []; function gtag(){dataLayer.push(arguments);} gtag('js', new Date()); gtag('config', 'UA-215686007-9'); </script> <script async src="https://pagead2.googlesyndication.com/pagead/js/adsbygoogle.js?client=ca-pub-9091845805741569" crossorigin="anonymous"></script> <script async custom-element="amp-ad" src="https://cdn.ampproject.org/v0/amp-ad-0.1.js"></script> <title>Zehabesha Ethiopian Reliable News Source – Truth Will Win