የወሎ ዕዝ አቶ እስክንድርን አልመረጥኩም ብሏል:

July 16, 2024
በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ አንድ የአማራ ፋኖ ማዕከላዊ እዝ እና ድርጅት ለመፍጠር ከሌሎች የፋኖ አደረጃጀቶች ጋር በመሆን የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል::
በዚህ ሂደትም እጩዎችን መመልመል ላይ የደረስን ሲሆን ከ 14 ያላነሱ የመመልመያ መስፈርቶች ተዘርዝረው ግማሽና ከዛ በላይ የሆኑትን ማለፍ ያልቻለው አቶ እስክንድር ነጋ ካልተመረጠ በሚል እሱና መሰሎቹ ዉይይት አቋርጠው ወጥተዋል::
በመሆኑም ይህ የተጀመረ ሂደት በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ አቶ እስክንድር ነጋ በአንድ አመት ጊዜ ዉስጥ ሶስተኛዉን የፋኖ ድርጅት እንደተለመደው እራሱን ዋና አዛዥ አድርጎ መመስረቱን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰምተናል::
ስለሆነም “የአማራ ፋኖ ትግል በቀዳሚነት ለአማራ ህዝብ ህልዉና” መሆኑን ለማይቀበልና ከዚህ ሰብአዊ ትግል ስሪት ዉጭ ለሆነ በአማራ ህዝብ የህልዉና ትግልና መስዋእትነት የዘመናት የስልጣን ጥሙን ለማርካት ለተነሳ ግለሰብ አሳልፈን መስጠት እንደሌለብን ስለምንረዳ በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰማው ነውረኛ ተግባር እንደሌለበት ለህዝባችን ማሳወቅ እንወዳለን::
ከዚህ ጋር ተያይዞም በቅርቡ በእውነተኛ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች እውነተኛ የአማራ ህዝብ ቤት እና ድርጅት ሰርተን እንደምንመጣ ለህዝባችን ለማብሰር እንፈልጋለን::
” አማራ በልጆቹ መስዋእትነት ይሻገራል::”
የአማራ ፋኖ ወሎ ዕዝ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአማራ ፋኖ በጎጃም አቶ እስክንድርን ምርጫ የለሁበትም ብሏል

Next Story

እየተሸረሽረ የመጣው የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ተዓማኒነት

Go toTop