የወንድማችን ግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል- ጠ/ሚ ዐቢይ

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ ፥“ሐሳብን በሐሳብ ማሸነፍ ያቃታቸው አካላት የወንድማችንን የግርማ የሺጥላን ነፍስ ነጥቀዋል” ብለዋል።
ልዩነትን በሠለጠነ መንገድ መፍታት ባህል በሆነበት ክፍለ ዘመን፣ በሐሳብ የተለየንን ሁሉ በጠመንጃ ለማሳመን መነሣት የጽንፈኝነት የመጨረሻው ጥግ ነው ሲሉም ገልጸዋል።
ተወልዶ ባደገበት አካባቢ፣ ከእኛ የተለየ ሐሳብ ማሰብ አልነበረበትም ብለው የሚያምኑ ነውጠኛ ጽንፈኞች የፈጸሙት አስነዋሪና አሰቃቂ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡
ጽንፈኝነትን በጊዜ ታግለን ካላስወገድነው ወደ መጨራረስ እንደሚወስደን ጉልሕ ማሳያ ነው ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።
Source:  Fana

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ከአማራ ክልል የወጡ አዳዲስ መረጃዎች! | ከይልቃል ከፋለ እና ጌታቸው ረዳ መተቃቀፍ ባሻገር!

Next Story

አቶ ግርማ የሺጥላን ጨምሮ አምስት ሰዎች በ“ኢ-መደበኛ ኃይሎች” መገደላቸውን የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ

Go toTop