የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ከምትገኘው ቆቦ ከተማ ለቅቆ መውጣቱን መንግሥት አስታወቀ።የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በትናንትናው ዕለት ነሐሴ 21፣ 2014 ዓ.ም እንዳስታወቀው “የህዝብን ፍጅት ለማስወገድ ሲባል” መከላከያ የቆቦ ከተማን መልቀቁን ገልጿል።
የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ “በጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማ መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የመንግሥት ኮሚዩኑኬሽን መግለጫ ህወሃት የቆቦ ከተማን ከውጭ “በብዙ አቅጣጫ” እያጠቃ አንደሆነ ገልጾ “የህዝቡን ደህንነት አደጋ ውስጥ በሚያስገባ መልኩ የከተማ ውስጥ ውጊያ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየፈጠረ ይገኛል” ብሏል።
በዚህም የተነሳ “መከላከያ የቆቦ ከተማን ለቆ ወደ ኋላ መጥቶ ለመከላከል የሚያስችለውን ወታደራዊ ይዞታዎችን ለመያዝ ተገዷል” ብሏል። የትግራይ ኃይሎች በበኩላቸው ባወጡት መግለጫ” የተከፈተባቸውን ጥቃት ለመከላከል በተደረገ የጸረ ማጥቃት ዘመቻ” የቆቦን ከተማን ጨምሮ ጉጉውዶ፣ ፎኪሳ፣ ዞብል፣ መንደፈራ፣ሮቢት፣ ሽዎች ማርያምና ተኮሎሽ የሚባሉ ስፍራዎችን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል።
DW