አሳፋሪው ‘ብልፅግና’ ያሬድ ሃይሌ

July 21, 2022

አጭበርባሪውና ኢሥነ- ሥርዓታዊው የ’ብልፅግና’ ቡድን ትላንት ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ. ም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አማራዎችን መሣርያ አስመዝግቡ ብሎ በመንጠቅ በማሰር እና ከ200 በላይ የአማራ አንቂዎችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በያሉበት እንደ አውሬ አድኖ በማፈን ሰብስቦ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በማቆየት በሌሊት አዋሽ ሰባት በተባለ ቦታ ወስዶ አጉሯቸዋል::

ከእነዚህም መካከል የባላገሩ ተሾመ ቤቱን ፈትሸው ባለቤቱን እንደወሰዷት በኦፊሴላዊ ፔጁ ገልፆታል::

የሚገርመው “በ2008 ዓ. ም አጋማሽ ከተለያዩ የ’ኦሮሚያ ክልል’ የሚኖሩ ቄሮዎች በአዲስ አበባ ከተ ከተማ ማ ተቃውሞ ሲያሰሙ ወያኔ- ኢህአዴግ ሀይል በመጠቀም 800 የሚሆኑ ቄሮዎችን በአዲስ አበባ በ10ሩ ክፍለ ከተማ ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች አጉሮ በሌሊት ያደረሳቸው አልታወቀም” በማለት መዘገባችን ይታወሳል:: ሆኖም ወያኔ ውድቀቱን አፋጠነበት እንጅ ያገኘው ትርፍ አልነበረም::

በተመሳሳይ ታዲያ የ’ኦሕዴድ ብልፅግና’ ከጡት አባቱ አለመማሩ አሳፋሪና አስነዋሪ ያደርገዋል:: ሕዝብን በሃይል አፍኘ እገዛለሁ: እዘርፋለሁ: አጭበረብራለሁ: አፋልሳለሁ ‘ኦሕዴድ ብልፅግና’ ነገ የሚያወራርደው የዞረ ድምሩ እንደሚሆን ጠንቁአይ ቤት መሄድ አይጠበቅብነም::

ወደር በሌለው ዘግናኝ ግፉ ሴት ወንድ: ሕፃን አረጋዊ: ጨቅላ ነፍሰ ጡር: ገበሬ ሹም:… የማይለየው ‘ብልፅግና’ በራሱና ባሰማራው ኦነግ ሸኔ: እንዲሁም ከጁንታው ስውር ሴራ ጋር በአማራ ብሔርና በኦርቶዶክስ ኃይማኖት አባቶችና ተከታዮች ላይ የሚያደርሰው ዘግናኝ ግፍ: ኢሰብአዊ ማፈናቀል: እስራት: ግድያ: ከሥራ ማፈናቀልና የመንጋ ወረራ: ቅጥ ያጣ ዝርፊያ በሕግ: በሕዝብ: በትውልድ: በታሪክ:… ተጠየቅ ማንቁርቱን የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም::

ምንግዜም ሕዝብ አሸናፊነው!

ውድቀት ለአፋኞች!

ሐምሌ 14 ቀን 2014 ዓ. ም

አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የአዲስ አበባ ባለቤት ማነው? (ስለ አዲስ አበባ ባለቤትነት በምሥጢር የቀረበ ሰነድ) – ኀይሌ ላሬቦ

Next Story

በግብፅ፣ በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማስፋት የታላቁ ህዳሴ ጉዳይን ለመፍታት ያስችላል ሲሉ የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ተናገሩ

Go toTop