“የብሄር ግጭት ተነሳ የሚባለው እርባና ቢስ ወሬ ነው። ከብልፅግና የሚጠበቀው በፅናት በመቆም ወደፊት መግፋት ብቻ ነው” – አቶ ብናልፍ አንዱአለም

July 3, 2022
የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሠባ ላይ የተናገረው
ሠላም በሌለበት ሀገር የሠላም ሚኒስትር የሆኑት አቶ ብናልፍ ሠሞኑን ሲካሄድ በቆየው የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሠባ ላይ የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ሂዴት በአግባቡ መረዳት የተሣናቸው ወገኖች ተጠባቂ የሆኑ ክስተቶችን እያነሡ የብሄር ግጭት ተነሣ ሠው ሞተ አያሉ ሲያብጠለጥሉ መሰማታቸው የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
የብሄር ግጭት ተነሳ የሚባለውን እርባና ቢስ ወሬ በመስማት ከአላማችን ማፈግፈግ ሳይሆን ከብልፅግና የሚጠበቀው በፅናት በመቆም ወደፊት መግፋት ነው በማለት እየተካሄደ ያለውን የዘር ማፅዳት፣ ማፈንና ማሠር ፓርቲያቸው አጠናክሮ ሊቀጥልበት እንደሚገባ በአፅንኦት መክረዋል።
አቶ ብናልፍ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ብልፅግናን በመወከል በጃቢ ጠና ወረዳ ለፓርላማ ተወዳድረው የነበረ ሲሆን የራሣቸው የብልፅግና መዋቅራቸው ሣይቀር መመረጥ የለባቸውም ብሎ ተቃውሟቸው ነበር።
ተቃውሞውን ወደ ጎን በማለት በግድ እንዲወዳደሩ ከተደረገ በኋላ ህዝቡም እሱን አንመርጥም ብሎ አቋም መውሠዱ ከተገመገመ በኋላ አቶ በላይነህ ክንዴ የሚባለው ባለ ሃብት ብናልፍ ወደቀ ማለት ጎጃም እንደ ወደቀ ነው የሚቆጠረው እያለ ለምርጫ ተወዳዳሪዎቹና ድምፅ ለሚሠጡ ሠዎች መደለያ አስራ ሁለት ሚሊዮን ብር መድቦ አከፋፍሎለት ተወዳድሯል።
ያሜ ሆኖ እንኳን ህዝቡ ሳይመርጠው ቀርቶ 183 ድምፅ ከተቃዋሚ ተወዳዳሪዎቹ በገንዘብ ድምፅ ገዝቶ በምርጫ ውድድሩ አልፏል ተብሎ ከአንድ ሣምንት በኋላ ተለጠፈለት።
በአካባቢው ህዝብ ዘንድ አንድ የሚታወቅ እና ሁሉም ሠው የሚግባባበት ሙድ ተይዛለች፤ 183 ከተባለ ብናልፍ አንዱአለም እንደማለት ነው።
እንዲህ አይነት ታሪክ ያለው ሠው በአብይ አህመድ ዘንድ እንደ አዋቂና ተንታኝ ተቆጥሮ ብናልፍ አንዳለው አየተባለ የትክክለኛነት ምሣሌ ተደርጎ ስትሠማ አይ ሀገር፣ አይ አማራ ከማለት ውጭ ምን ይባላል?

ፈለገ ግዮን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አዲስ አበባ ያለው የኦነግ ቢሮ በኦነግ ሸኔ ላይ እየተወሰደ ነው ያለው ወታደራዊ እርምጃ እንዲቆም ጠየቀ

Next Story

መስጠት ብቻ ወይንስ ስጥቶ መቀበል? (ጥሩነህ)

Go toTop