ተቃዋሚው የአፋር ህዝብ ፓርቲ በብሔራዊ ምክክር ላይ ለመሳተፍ እንደሚቸገር አስታወቀ።

June 1, 2022
ፓርቲው ትናንት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ የሀገሪቱ ወቅታዊና ዘላቂ ያላቸው ችግሮች «ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በፍትሃዊ፤ ሀቀኛ፤ ተዓማኒ፤ ግልፅ እና ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ምክክር መፈታት አለበት» ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል። ሆኖም «ዝቅተኛ መስፈርቶችን ያላሟላ »ሲል የገለጸው ምክክሩን የሚመራው ኮሚሽን ፣«ትጥቅ ያነሱ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ» ያላቸው ኃይሎችን አንድ ላይ አምጥቶ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የማይችል በመሆኑ ጊዜና ጉልበት ከማባከን ውጭ መፍትሄ ያመጣል ብለን አናስብም ብሏል። «ችግሮቹን አስተካክለን ሀገራችንን በቅንነት እንታደግ ሲል በተደጋጋሚ መጠየቁን ያስታወሰው የአፋር ህዝብ ፓርቲ ኮሚሽኑ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች እስኪያሟላ ድረስ በሂደቱ ለመሳተፍ እንደሚቸግረው አስታውቋል። ፓርቲው ከዚህ ሌላ መንግሥት ህዝቡን ለአደጋ በሚያጋልጡ ተግባራት ላይ ተሰማርቷል ሲልም ከሷል። ኢትዮጵያን በሚመራው «በብልጽግና ፓርቲ እና በህወሓት የስልጣን ጥማት» ሲል በገለጸው ምክንያት የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአፋር ህዝብ ያልተገባ ያለውን የሕይወትና የሀብት ዋጋ ለመክፈል መገደዱን ጠቅሶ አሁንም በገዛ መሬቱ በየቀኑ እየተገደለ ይገኛል ብሏል። ፓርቲው በክልሉ የኑሮ ውድነት፤ሙስናና የመልካም አስተዳደር እጦት ፣እንዲሁም ከፍተኛ የውኃ እጥረት መኖሩንም ጠቅሷል። በተለይ የውኃ መስመር ዘግተው ውኃ እየሸጡ ህዝቡን ለከፍተኛ የውኃ ጥም አጋልጠዋል ያላቸው ባለስልጣናት ፈጽመዋል ያለው «ይቅር የማይባል የሰብዓዊ መብት ጥሰት» በፍጥነት መስተካከል እንደሚገባውም አሳስቧል።
DW

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

የክህደት ጥግ ሲጋለጥ….!

Next Story

የቀጠለው ድርድር

Go toTop