እናት ፤ ልክ እንደ ለም መሬት
መሐፀኗ ፤ አብቃይ ነው ሰውነት ፡፡
ይኽ የዓለም ህዝብ ፤ ወንድ ና ሴት
ከእናት መሐፀን የወጣ ነው በራቁትነት ፡፡
እናት …
ወድና ሴትን አፈራች …
በማሃፀን በደም ስሯ እያጠባች ፡፡
ዘጠኝ ወር በመሐፀኗ ተሸክማ
በጭንቅ ዓምጣ የወለደች …
ጡቷን አጥብታም ያሳደገች ፡፡
እናት …
ፍቅር ናት ፡፡
ብሽቅ ፖለቲካ ፤ የማይነካካት …
የዓለም ዜጋነት ።
ዓለምን አቃፊነት
ድንበር የማይገድባት
ፍቅር ብቻ የሚገዛት
እንዲህ ናት… እናት ።
አባታዊ አምባገነንት
ሲያልፍም አይነካት ፡፡
ሚያዚያ 30 ቀን /2014 ዓ/ም ( ለእናቶች ቀን መታሰቢያ ይሁንልኝ )