![](https://cdn.statically.io/img/amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/04/279351965_293336919656437_2813429300688993227_n.jpg?quality=100&f=auto)
የሸኔ ቡድን በወረዳው የሕዝቡን ንብረት በመዝረፍ እና የሰላማዊ ሰዎችን ሕይወት በከንቱ በመቅጠፍ ኅብረተሰቡን አደጋ ላይ መጣል ከጀመረ ረጅም ጊዜ አስቆጥሯል።
ይህ ድርጊት ያማረራቸው የዳኖ ወረዳ ነዋሪዎች በአንድነት በመውጣት ሸኔን የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።
ሰልፈኞቹ መንግሥት በሽብር ቡድኑ ላይ የሚወስደውን እርምጃ እንደሚደግፉ እና ኅብረተሰቡን መሸሸጊያ ያደረጉ አባላቱን ለማጋለጥ ዝግጁ መሆናቸውን አሳይተዋል።
(ኢ.ፕ.ድ)
![](https://cdn.statically.io/img/amharic-zehabesha.com/wp-content/uploads/2022/04/279093189_293336882989774_3095078996412058998_n.jpg?quality=100&f=auto)