አንበሳ ፋርማሲ የአገሪቱ መዲና በሆነችው በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እድሜ ጠገብ የታሪክ አሻራችን ብቻ አይደለም፡፡በአይነቱ ብቸኛ የሆነ፣ በሀኪሞች ታዝዘው በባለሙያወች ተዋህደውና ተቀምመው ፈውስ የሚሆኑ የአያሌ በሽታወችን የሚያድኑ መድሀኒቶች መቀመሚያ ፋርምሲም ነው፡፡ ይህ አገልግሎቱ አንበሳ ፋርማሲን በአይነቱ ብቸኛ አድርጎት እስካሁን ድረስ ለህዝቡ ምትክ የለሽ የጤና አገልግሎትን እየሰጠ ይገኛል፡፤
ከጤና አኳያ ስለፋርማሲው ምትክ የለሽነት እኔ ራሴ ምስክር ነኝ፡፡ ይዞኝ የነበረውን የቆዳ በሽታ ብዙ ጥሬ ጥሬ ሳይሳካልኝ ቀርቶ መጨረሻ ላይ በሀኪም ትእዛዝ ከዚህ ፋርማሲ ተቀምሞ የተሰጠኝ መድሀኒት ነው ያዳነኝ፡፡ ይታያችሁ ለአዲስ አበቤ ሰው በተለይ ዛሬ ላይ ያህንንን ማጣት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፡፡
ህዝብ ሲጠቀም የሚያመው መንግስት፣ የህዝቡ ጤና ሲጠበቅ ህመም የሚሰማው መንግስት፣ የህዝቡ ሰላም መሆን የሚያሰጋው መንግስት ጸረ ህዝብነቱ፣ ተረኝነቱ፣ አድሏዊነቱ፣ ማናአለብኝነቱና በጥጋብ እብጠቱ ጫፍ ደርሷል፡፡ ፋርማሲውን አፍርሶ ኦቦ ጀርመን አመንቲ የተባለ ተረኛ ባለሀብት ህንጻ ሰርቶ በማከራየት ቢዝነስ እንዲሰራበት ቦታውን ከአንበሳ ፋርማሲ ቀምቶ ለኦቦ አመንቲ ሊሰጠው እንደሆነ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡
በከተማዋ ውስጥም ሆነ በአገሪቱ ውስጥ ኦሮሙማ የሚሰራቸው ጸረ ህዝብና ጸረ አገር አብሮ የማያኗኑሩ ስራወች ተዘርዝረው አያልቁም፡፤ ጥጋቡና ማንአለብኝነቱ እየባሰበት ሄዷል፡፡ መቆሚያም ያለውም አይመስልም፡፡ይህ ጥጋብና እብ ጠት ሊፈነዳ ደርሷል፡፡ ፍንዳታውም ለብዙ ይተርፋል፡፡ እንኳን እንደዚህ በዘረኝነት መጠኑን አልፎ በከረፋና በከፋ የተግማማ የፖለቲካ ስርአት ቀርቶ በበሰለ ህዝባዊ አመራርም ቢሆን የህዝብ ብሶትና ግፍ ሞልቶ ከፈሰሰ የሚያቆመው የለም፡፡
አንበሳ ፋርማሲን አትንኩ፡፤ የህዝብ ጤና መጠበቂያ ምትክ የለሽ ፋርማሲ ነው፡፡ታሪክ ያለን ህዝብ ስለሆንና ታሪክም ስለምናውቅ ስለፋርማሲው የታሪክ አሻራነት ተረኞችን ለማስረዳት አንሞክርም፡፡ ታሪክ ደግሞ በተረኝነት አይሻርም፡፡ አይቀየርም፡፡