የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከልክሏል! # አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ያለው ልብስም ተከልክሏል!

March 15, 2022

#ዜና #መረጃ
# የአጼ ምኒልክ ምስል ያለው ልብስ እንዳይለበስ

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአጼ ምኒልክ ምስል እና ኮከብ የሌለው አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይያዝ በይፋ መከልከሉን ተማሪዎች ገለፁ፡፡ “ ነፍጠኛ ዳውን ዳውን” በማለት ሰሞኑን ቪዲዮ ቀርፀው በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለቀቁት ኦሮምኛ ተናጋሪ ተማሪዎች ጥያቄ መሠረት፣ የዩኒቨርስቲው አስተዳደር በሰጠው ውሳኔ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የአጼ ምኒልክ ምስል ያላቸውን ማናቸውም ልብሶች መልበስ የተከለከሉ መሆኑን፣ በተጨማሪም ኮከብ የሌለውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቅ ዓለማ መያዝ እንደማይችሉ ገልጾ፣ ውሳኔውን በጽሁፍ አስፍሮ በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ ለጥፏል፡፡
በዚህ ውሳኔ የልብ ልብ ያገኙ ተማሪዎች፣ “ነፍጠኛ ዳውን ዳውን ” የሚለውን መፈክራቸውን ከማጠናከራቸውም ባሻገር፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ያለውን ማንኛቸውን ልብስ ለብሶ የሚያገኙትን ተማሪ እስከ መደብደብ ደርሰዋል፡፡ ሌላው ቀርቶ፣በዊልቸር የሚሄድ አንድ ተማሪ የአጼ ምኒልክ ምስል ያለበትን ቲሸርት ለብሶ በመገኘቱ ከበድ ያለ ድብደባ ደርሶበታል፡፡ ማታ ማታም በየዶርሙ እየዞሩ፣ “የአማራ ተማሪዎች ውጡ” በማለት ከፍተኛ ረብሻ ሲፈጥሩ ሰንብተዋል፡፡
ድብደባውን እና ሁከቱን የሚፈጽሙት ተማሪዎች ይፋዊ ባልሆነ መንገድ “የመንግሥት ድጋፍ አለን” ብለው ስለሚተማመኑ፣ ለሕግ ተገዢ ለመሆን ፈጽሞ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ብዙሃኑ ተማሪዎች ይናገራሉ፡፡ በትላንትናው ምሽት ግቢውን ለቀው የወጡት ተማሪዎች የአማራ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ፣ በረባሽ ተማሪዎቹ እና ሕግን ማስከበር በተሳነው የዩኒቨርስቲ አስተዳደር የተበሳጩ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ተማሪዎች ናቸው፡፡
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በዛሬው ዕለት የመማር ማስተማሩ ሂደት ከሞላ ጎደል ቆሟል የሚባልበት ደረጃ ላይ ሲሆን፣ ትላንት አብዛኛው ተማሪ በግቢው ውስጥ አላደረም፡፡ ዛሬም በአብዛኛው ወደ ክፍል ገብቶ ትምህርቱን አልተከታተለም፡፡

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

አሳፋሪው የብልጽግና የምርጫ ሂደት – በጌትነት ከበደ

Next Story

አሸባሪው ሕወሓት የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል በመሸሽ በሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች አማራ ክልል ገብተዋል

Go toTop