የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ
ኢትዮጵያ ”ወላሂ ኢትዮጵያን እወዳታለሁ“ የሚለው ንግግሯ በሁላችንም ልብ ታትሟል፡፡ የአፋርን ልዩ ኃይል ስትቀላቀል ስምንተኛ ክፍለ ነበረች፡፡ ህዋኃት አፋርን ሲወር ከሀገር በላይ ምንም የለም በማለት ደብተሯን አስቀምጣ፣ ጠመንጃ በመያዝ ህወኃትን ፊት ለፊት ተጋፍጣለች ፣ የአፋሯ ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድ ፡፡
ሀዋ ካደገችበት ቀየዋ ብቻ በአሸባሪው ህዋሃት 58 ሰዎች ተገድለዋል፣ከመቶ በላይ ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ሀዘኑ ገና ከልቧ ባይወጣም ህዋሃትን ለመታገል ግን አሁንም ቁርጠኛ ነኝ
ትላለች፡፡
”ኢትዮጵያን ከልቤ እወዳታለሁ፣ አሁንም ቢሆን መስዋእት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ“ የምትለው ጀግናዋ የአፋር ልዩ ኃይል በጦርነት ወቅት በደረሰባት ጉዳት አልፎ አልፎ ይጥላታል፡፡
”አይኔም እንደቀደመው ማየት ተስኖታል“ ትላለች ፡፡ ትናንት ለብዙዎች ነጻነት የተዋደችው ሐዋ፤ ከህመሟ አገግማ ትምህርቷን መቀጠል እና ኢንጅነር መሆን የወደፊት ህልሟ ነው፡፡ ሐዋ የእኛን ህመም ነው የታመመችው ፡፡ የደማችውም፣ የቆሰለችውም ለእኛ ነጻነት ነው፡፡ ስለሆነም በቃል ሳይሆን በተግባር ኢትዮጵያን እንወዳለን የምንል ሁሉ ከጀግናዋ የአፋር ልዩ ኃይል ሐዋ መሀመድን ጎን በመቆም አለኝታነታችንን እናረጋግጥ፡፡